loading
በኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት የሚመራበት የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት የሚመራበት የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው፡፡
በኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት የሚመራበት ስርዓት ባለመኖሩ በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ወደ ጎረቤት ሀገራት እየሄዱ ለመስራት ሲገደዱ ተስተውሏል፡፡
ይህንን ችግር ለመቅረፍና ከዩኒቨርሲቲዎች በየጊዜው ተመርቀው የሚወጡ ወጣቶች ዲጂታል ኢኮኖሚው ውስጥ ገብተው ሃብት እንዲያፈሩ ለማድረግ መደላድል ለመፍጠር ያስችል ዘንድ ‹‹የኤሌክትሮኒክስ ትራንዛክሽን አዋጅ›› ተረቅቆ ውይይት እየተደረገበት ነዉ፡፡
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በተዘጋጀው በዚህ ረቂቅ አዋጅ ውይይት ላይ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች፤ ባንኮች እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው ስርዓት ቀድመው ሃብት ያፈሩ ሰዎችን እንጂ እውቀት ላላቸው ሰዎች አሰሪ አይደለም ያሉት ኢኖቬሽንና ቴክሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር እንጂነር  ጌታሁን መኩሪያ ቴክሎጂ ለመጠቀም ዝግጁ የሆነውን ወጣት የሚያስራ ስርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ ስርዓቱ የሚመራበትና ውድድርን የሚያበረታታ ህጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት አንዱ ነው፡፡
የህግ ማዕቀፉ የኤሌክትሮኒክ ግዢና ሽያጭ፤ የኤሌክትሮኒክስ ፊርማ፤ ደረሰኝ፤ መልዕክት ና የመንግስት አገልግሎቶችን የሚያጠቃልል ነው፡፡
በአለማችን ወደ 6 ትርሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በኤሌክትሮኒክስ ግብይት እንደሚዘዋወር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *