በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ መቐለ ከጅማ አባ ጅፋር ይጫወታሉ
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ መቐለ ከጅማ አባ ጅፋር ይጫወታሉ
የሊጉ የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ተስተካካይ ጨዋታ በመቐለ 70 እንደርታ እና ጅማ አባ ጅፋር መካከል ትግራይ ስታዲየም ላይ ቀን 9፡00 ላይ ይጫወታሉ፡፡
በአሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ የሚሰለጥኑት መቐለ፤ በተከታታይ ስምንት ጨዋታዎች ላይ ድልን ያሳኩ ሲሆን ዘጠነኛውን ድል በጅማው ቡድን ላይ በመቀዳጀት የሊጉን መሪነት ከተከታዮቻቸው በነጥብ ርቀው ያስቀጥላሉ የሚል ሰፊ ዕድል አግኝተዋል፡፡
ይሁን እንጂ አስተዳደራዊ ችግሮቹን እየፈታ እንደሆነ የሚነገርለት ጅማ አባ ጅፋር በቅርብ ካስመዘገባቸው ውጤት አንፃር ለትግራዩ ቡድን በቀላሉ እጅ ይሰጣል ብሎ አይጠበቅም፡፡
ይህ ተስተካካይ ጨዋታ በ11ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መደረግ የነበረበት ቢሆንም ጅማ አባ ጅፋር በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመልስ ጨዋታ ወደ ሞሮኮ በማቅናቱ ምክንያት ያልተካሄደ ጨዋታ ነው፡፡
ሊጉን መቐለ 70 እንደርታ በ32 ነጥቦች ሲመራ፤ ሲዳማ ቡና በ30 ሁለተኛ ነው፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ26 ሶስተኛ፤ ፋሲል ከነማ በ25 አራተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ በ22 ነጥቦች ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
ደቡብ ፖሊስ፣ ስሑል ሽረ እና ደደቢት ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ፡፡