loading
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማ አባ ጅፋር እና ፋሲል ከነማ ዛሬ ይጫወታሉ፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማ አባ ጅፋር እና ፋሲል ከነማ ዛሬ ይጫወታሉ፡

 

 

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ አንድ ጨዋታ ዛሬ ቀን 9፡00 ሲል ጅማ አባ ጅፋር በጅማ ስታዲየም የጎንደሩን ፋሲል ከነማ ያስተናግዳል፡፡

 

 

ጅማዎች ከአስተዳደር ችግሮች መልስ በሊጉ ድል እያደረጉ ሲሆን የዛሬው ጨዋታ ላይ ድልን ማሳካት ከቻሉ፤ ወደ ሊጉ መሪዎች የሚያስጠጋቸው በመሆኑ ሜዳቸው ላይ የሚደርጉትን የቤት ስራ መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

 

 

 

በአንፃሩ አፄዎቹ ድል የሚቀናቸው ከሆነ ደግሞ የሊግ ደረጃቸውን ወደ ሶስተኛ ከፍ ማድረግ ይቻላቸዋል፡፡
የሊጉ የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ተስተካካይ ጨዋታ፤ በመጪው ሐሙስ የካቲት 21/2011 ዓ/ም በትግራይ ስታዲየም መቐለ 70 እንደርታ እና ጅማ አባ ጅፋር መካከል ይደረጋል፡፡

 

 

 

የሊጉን የደረጃ ሰንጠራዥ መቐለ 70 እንደርታ በ32 ነጥብ ሲመራ፤ ሲዳማ ቡና በ30 ይከተላል፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ26 ነጥብ ሶስተኛ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ፋሲል ከነማ በዕኩል 24 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው 4ኛ እና 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

 

 

ደቡብ ፖሊስ፣ ስሑል ሽረና ደደቢት አሁንም ወራጅ ቀጠናን የሙጢኝ ብለዋል፡፡

 

 

 

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ምንይሉ ወንድሙ ከመከላከያ በ11 ጎሎች ሲመራ፤ አማኑኤል ገብረሚካኤል ከመቐለ 70 እንደርታ እና አዲስ ግደይ ከሲዳማ ቡና በ10 ጎሎች ይከተላሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *