loading
በእንግሊዝ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን የሀገሪቱ የጤና ሃላፊ አስታወቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2013 በእንግሊዝ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን የሀገሪቱ የጤና ሃላፊ አስታወቁ፡፡የእንግሊዝ ጤና ሃላፊ ማት ሃንኮክ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ ጫፍ ላይ መድረሱን የተናገሩ ሲሆን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ተጨማሪ ክልከላዎች ሊተገበሩ ይገባል ብለዋል፡፡አሁን ላይ ያለን ምርጫ ክልከላዎችን በማያከብሩ ሰዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመር አለብን ብለዋል ዋና ፀሐፊው፡፡

በመንግስት በኩል የተቀመጡ የጥንቃቄ እርምጃዎችንና ክልከላዎችን ሰዎች ባለማክበራቸው የቫይረሱ ስርጭት መስፋፋቱ ነው የተነገረው፡፡እንደ ቢቢሲ ዘገባ የሀገሪቱ መንግስት በኮቪድ 19 ተጠርጥረው እራሳቸውን ማግለል ሲገባቸው ይህንን ተግባራዊ በማያደርጉት ላይ እስከ አስር ሺህ ፓውንድ የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት አስቀምጧል፡፡እንግሊዝ ባሳለፍነው እሁድ ብቻ ከ3 ሺ 8 መቶ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዘባት ሲሆን የሟቾች ቁጥርም በ18 አሻቅቧል፡፡

የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ሁለተኛው ዙር የኮቪድ 19 ስርጭት እየመጣ ነው ሲሉ አስጠንቅቀው መንግስት ስርጭቱን ለመቀነስ ጠንካራ እርምጃዎችን መውሰድ ይጠበቅበታል ብላዋል፡፡የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማበልፀግ እንግሊዝ፣ ቻይና ፣ሩሲያና አሜሪካ ከጊዜ ጋር እሽቅድምድም ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *