loading
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ታላላቅ ቡድኖች በሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፈዋል

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ታላላቅ ቡድኖች በሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፈዋል

 

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት መርሀግብር ትናንት ምሽት በርካታ ጨዋታዎች ተከናውነዋል፡፡

ተጠባቂ በነበረው የለንደን ደርቢ ጨዋታ ቼልሲ ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ ቶተንሃምን 2 ለ 0 ረትቷል፡፡ የሰማያዊዎቹን የድል ጎሎች ፔድሮ ሮድርጊዝ እና የስፐርሶች ተከላካይ ኬራን ትሪፒየር ከመረብ አገናኝተዋል፡፡

 

የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ዋትፎርድን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲረታ ሳዲዮ ማኔ እና ቨርጂል ቫን ዳይክ ሁለት ሁለት ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፉ፤ በፊርሚኖ ቦታ የመሰለፍ ዕድል የተሰጠው ኦሪጊ ሌላኛዋን አስቆጥሯል፡፡

የፔፕ ጓርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ ኢቲሃድ ላይ ዌስት ሃምን በሰርጂዮ አጉዌሮ ብቸኛ የፍፁም ቅጣት ምት ጎል 1 ለ 0 ድል አድርጓል፡፡

አርሰናል ቦርንመዝን ኤመሬትስ ላይ 5 ለ 1 ረምርሞታል፡፡ ከዩናይ ኢመሪ ጋር የተጎራበጠው ኦዚል፣ ሚኪታሪያን፣ ኮሴዬልኒ፣ ኦባማያንግ እና ላካዜት የግቦቹ ባለቤቶች ናቸው፡፡ ሊስ ሙሴ ለቦርንመዝ ማስተዛዘኛዋን ከመረብ አገናኝቷል፡፡

በርካታ ተጫዋቾቻቸውን በጉዳት ምክንያት ወደ ለንደን ይዘው ያልተጓዙት ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ሴል ኽረስት ፓርክ ላይ ክሪስታል ፓላስን  3 ለ 1 ድል አድርጓል፡፡ ለዩናይትድ ቤልጅየማዊው ሮሜሉ ሉካኩ ሁለት ግቦችን ሲያበርክት፤ አሽሊ ያንግ የማሳረጊያዋን ጨምሯል፡፡  ዋርድ የፓላስን አንድ ግብ አስቆጥሯል፡፡

ሳውዛምፕተን ሴንት ሜሪ ላይ ፉልሃምን በሮሜዩ እና ዋርድ- ፕራውስ ጎሎች 2 ለ 0 ድል አድርጓል፡፡

ሊቨርፑል በ69 ነጥብ የፕሪምየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠራዥ አናት ላይ ሲቀመጥ፤ ሲቲ በ68 ይከተላል፤ ቶተንሃም በ60 ሶስተኛ፣ አርሰናል በ56 4ኛ፣ ማንችስተር ዩናይትድ በ55 5ኛ እንዲሁም ቼልሲ በ53 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *