loading
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ቼልሲ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን ሲያረጋግጥ፤ ማንችስተር ዩናይትድ በውድድሩ እንደማይሳተፍ ተረጋግጧል

የ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ከዓርብ ጀምሮ እየተካሄዱ ነው፤ ዛሬ ምሽት በሚካሄድ የማሳረጊያ ጨዋታም ይቀጥላል፡፡

የመርሲ ሳይዱ ሊቨርፑል ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም አምርቶ ኒውካስትል ዩናይትድን 3 ለ 2 በመርታት አስፈላጊ ውጤት አስመዝግቧል፤ ዛሬ ምሽት ማንችስተር ሲቲ ጨዋታውን እስኪያደርግ ድረስ የሊጉን የደረጃ ሰንጠራዥ በ94 ነጥብ እየመራ ይገኛል፡፡ ለቀያዮቹ ቨርጂል ቫን ዳይክ፣ መሀመድ ሳላህ እና ዲቮክ ኦሪጊ አስቆጥረዋል፡፡

ቅዳሜ ዕለት በጠራራ ፀሀይ የማውሪሲዮ ፖቼቲኖው ቶተንሃም ሆተስፐር ወደ ዲን ኮርት አምርቶ ውድ ሶስት ነጥብ ለቦርንመዝ አስረክቦ ተመልሷል፡፡ በዚህም ስፐርስ ሙሉ ለሙሉ የቀጣይ ዓመት የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ለማግኘት የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታውን ይጠብቃል፡፡

ትናንት ቼልሲ በስታንፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ዋትፎርድን አስተናግዶ ሎፍተስ ቺክ፣ ዳቪድ ሊዩዝ እና ጎንዘሎ ሂጉዬን ባስቆጠሯቸው ጎሎች 3 ለ 0 በመርታት በ71 ነጥብ የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን አረጋግጧል፡፡ እንግሊዛዊው ጋሪ በቼልሲ ማሊያ የመጨረሻ ጨዋታውን አድርጎ ሽኝት ተደርጎለታል፡፡

 ወደ ጆን ስሚዝ ያመራው የኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ማንቼስተር ዩናይትድ ሀደርስፊልድ ታውንን በስኮት ማክቶሚናይ ግብ ቀዳሚ መሆን ቢችልም አይዛክ ምቤንዛ ያሰገኛት ጎል ከሊጉ የተሰናበተው ቡድን ሀደርስፊልድ በሜዳው ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል፡፡

ዩናይትድ አሁን ያለው ተስፋ ዩሮፓ ሊግ ብቻ ይሆናል፡፡

አርሰናልም በሜዳው ኤመሬትስ ተጫውቶ ነጥብ ጥሏል፤ የዌልሱ ካርዲፍ ሲቲ ቅዳሜ በክሪስታልፓላስ 3 ለ 2 ውጤት መረታቱን ተከትሎ ካርዲፍ ከሊጉ የተሰናበተ ሶስተኛው ቡድን ሲሆን ብራይተኖች ከመድፈኞቹ ጋር ከስጋት ነፃ ሁነው ጨዋታቸውን አድርገው አንድ ነጥብ ይዘው ተመልሰዋል፡፡

መድፈኞቹ በጋቦናዊው ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ የፍፁም ቅጣት ግብ በ9ኛው ደቂቃ ቀዳሚ ቢሆንም በሙራይ የፍፁም ቅጣት አቻ ሁነዋል፡፡

ይህን ተከትሎ አርሰናል በ67 ነጥብ እና 20 ንፁህ ጎሎች አምስተኛ ደረጃ ላይ እንዲሁም ሌላኛው የሰሜን ለንደን ክለብ ቶተንሃም በ70 ነጥብ እና 28 ጎሎች አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል መድፈኞቹ አራተኛ ሁነው ለማጠናቀቅ ቶተንሃም ተሸንፎ አርሰናል ያለውን ንፁህ ጎሎች ከስፐርስ ማስበለጥ ይኖርበታል፡፡

ዛሬ ምሽት 4፡00 ላይ ደግሞ ማንችስተር ሲቲ በኢቲሃድ ሌስተር ሲቲን ያስተናግዳል፤ ኬቨን ዴ ብሯይኔ ጨዋታው እንደሚያመልጠው ሲነገር የአማካዩ ፈርናንዲህኖ አጠራጣሪ ሲሆን በቀበሮዎቹ በኩል ዳንዬል አማርቲ እና ማት ጀምስ የማይኖሩ ይሆናል፡፡

የፔፕ ጓርዲዮላው ሲቲ 92 ነጥብ ይዞ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *