loading
በኦህዴድ 9ኛ ጉባዔ ላይ የተሳተፉት በኦሮሞ ስም የተደራጁ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለኦሮሞ ህዝብ በአንድነት እንሰራለን አሉ

አርትስ 09/01/2011
የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በጅማ ከተማ በመካሄድ ላይ በሚገኘዉ 9ኛዉ የኦህዴድ ጉባዔ ላይም ንግግር አድርገዋል፡፡
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ህዝብ ግንኙነት ሃላፊዉ አቶ ኢብሳ ነገዎ ባደረጉት ንግግርም ሰሞኑን ሃላፊነት በማይሰማቸዉ አካላት የተፈጠሩት ችግሮች እኛን አይወክሉም ፤ስም የማጥፋት ዘመቻ ተካሂዶ በክፉ ሲያነሱን ሰምተናል፤ ነገር ግን ጉዳዩ ድርጅታችንን አይመለከትም ብለዋል፡፡
የህግ የበላይነቱ ኦሮሞን የሚጎዳ ከሆነና ያለፈዉን ጨቋኝ ስርአት የሚመልስ ከሆነ እንታገላለን አሁን ባለዉ ሁኔታ ግን ኦህዴድን የምናግዝበት ቦታና ሁኔታ አለ ሲሉ አቶ ኢብሳ ተናግረዋል፡፡
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ በበኩላቸዉ አንድነት ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በብሄሮች መካከል የሚፈጠር ልዩነት ማብቃት አለበት፤ በጥላቻ መንገድ መሄድ ትርፉ ኪሳራ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ፓርቲ ሊቀመንበርና መስራቹ ዶ/ር ዲማ ነገዎ በንግግራቸዉ 9ኛዉ የኦህዴድ ጉባኤ እየተካሄደ ያለዉ በወሳኝ ሰዓት ነዉ ያሉ ሲሆን ሁሌም በኦሮሞ ስም የተደራጀን ፓርቲዎች አንድ መሆን ይጠበቅብናል፤ አንድነታችን ደግሞ የአሁኑን ለዉጥ ለማደናቀፍ እየተደረገ ያለዉን እንቅስቃሴ መግታት እንድንችል ያደርገናል ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *