loading
በኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች የቤት ለቤት የኮሮና ቫይረስ ልየታ ተጀመረ::

በኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች የቤት ለቤት የኮሮና ቫይረስ ልየታ ተጀመረ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2012 በደቡብ  ክልል  የትራንስፖርት  እገዳው  ማሻሻያ ተደረገበትየኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል በደቡብ ክልል በሕዝብ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ክልከላ ማሻሻያ እንደተደረገበት የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አስታወቀ።ማሻሻያው ተግባራዊ የሚደረገው በመናኸረያዎች አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ሲረጋገጥ እንደሆነም ተመልክቷል። የቢሮው ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ-ሀይል የኅብረተሰቡን ተጋላጭነት ለመከላከል የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች ዝግ እንዲሆኑ አድርጎ ቆይቷል።“ነገር ግን በፌዴራል ደረጃ የቫይረሱን ወረርሽኝ ለመከላከል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመታወጁና እስከ ክልል ባለው መዋቅር ወጥ ውሳኔ እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ማሻሻያ ማድረግ አስፈልጓል” ብለዋል፡፡

በዚህም መሰረት ከየትኛውም አካባቢ ወደ ክልል የሚንቀሳቀስ ሀገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከመጫን አቅሙ ግማሹን በመቀነስ መንቀሳቀስ እንደሚችል ገልጸዋል።የከተማ አውቶብስ፣ የግል ተሽከርካሪዎች፣ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተሸከርካሪዎችም እንዲሁ ከዚህ በፊት ከሚይዙት ተሳፋሪ በግማሽ ቀንሰው እንዲጭኑ ተወስኗል ነው ያሉት።“የባለ 2 እግር ሞተር ሳይክል፣ ባለሶስት እግር ባጃጆችና የከተማ ታክሲ አገልግሎት ቀደም ሲል በክልሉ በግብረ-ሀይሉ የተላለፈው ውስኔ እንደተጠበቀ ሆኖ የሚሰሩ ይሆናል” ብለዋል።መናኸሪያዎችም ተከፍተው ስራ የሚጀምሩት ለተሳፋሪው የእጅ መታጠቢያ ስፍራና አስፈላጊ ቁሳቁስ መሟላታቸው ሲረጋገጥ እንደሆነ ተናግረዋል።በተጨማሪም መንገደኞች ወደ መናኸሪያ ሲገቡና ሲወጡ የሙቀት ልኬት ማከናወን የሚያስችል ልኬታቸው አጠራጣሪ ሲሆን ለይቶ ለማቆያ ስፍራዎች መዘጋጀት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።በተሽከርካሪዎቹ የኬሚካል ርጭት ማድረግ፣ በቫይረሱ ዙሪያ በሚኒ ሚዲያ የማስተማር ስራ መስራት እንዲቻል አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸው ተገምግሞ በቀጣይ ሶስት ቀናት ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎቱ እንደሚጀመር አቶ ማስረሻ ገልጸዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *