loading
በካሊፎርኒያው ሰደድ እሳት የሟቾች ቁጥር ጨምሯል

አርትስ 04/04/2011

 

በካሊፎርኒያ ግዛት ታሪክ ታይቶ አያውቅም በተባለለት እሳት አደጋ እካሁን የ42 ሰዎች ህይዎት ተቀጥፏል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው 228 ሰዎች እስካሁን የገቡበት አልታወቀም፤ 15 ሺህ ሰዎች ደግሞ በከፍተኛ የአደጋ ስጋት ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ከ7 ሺህ 200 በላይ  ቤቶችን ያወደመው ሰደድ እሳት 250 ሺህ የሚሆኑ ነዋሪዎችን አካባቢያቸውን ለቀው  እንዲፈናቀሉ አስገድዷቸዋል ብለዋል የአካባቢው ባለስልጣናት፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በሀገሪቱ ከፍተኛ አደጋ መከሰቱን ይፋ አድርገው ተጎጂዎችንና ቤተሰቦቻቸውን የሚያፅናና መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በካሊፎርኒያ የአየር ጸባይ ለውጥ መከሰቱና ከፍተኛ የሆነ ሙቀት ማስከተሉ አንዲሁም  የዝናብ መጠን መቀነስ ለአደጋው መንስኤ ስለመሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *