በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የግብፁ አል አህሊ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ተቀላቅሏል፡፡
አርትስ ስፖርት 13/01/2011
የካፍ ቶታል ቻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ከትናንት በስቲያ እና ትናንት ተከናውነዋል፡፡
በዚህም አርብ ዕለት ዋይዳድ አትሌቲክ ክለብ ከ ኢ.ኤስ ሴቲፍ 0 ለ 0 አቻ ሲለያዩ፤ ኢስፔራንስ አትዋል ዱ ሳህልን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ቲፒ ማዜንቤ ከ አንጎላው ዴስፖርቲቮ ዴ አጎስቶ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡
በዚህም መሰረት በአጠቃላይ ዴስፖርቲቮ ዴ አጎስቶ፤ ሴቲፍ እና ኢስፔራንስ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ሲቀላቀሉ ትናንት ምሽት በተደረገ ሌላ ጨዋታ አል አህሊ ሆሮያን በመርታት ወደ ተከታዩ ዙር ማለፍ ችሏል፡፡
በዚህም በግማሽ ፍፃሜ አል አህሊ ከ ሴቲፍ እንዲሁም አጎስቶ ከ ኢስፔራንስ ጥቅምት 13/2011 ዓ/ም ይጫወታሉ፡፡
በካፍ ኮንፌዴሬሽን ደግሞ ዛሬ የሩብ ፈፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ሲደረጉ፤ ኢኒየምባ ከ ራዮን ስፖርትስ 10፡00 ስዓት፤ ራጃ ካዛብላንካ ከ ካራ ብራዛቪል ምሽት 1፡00 ስዓት፤ እንዲሁም በተመሳሳይ ምሽት 4፡00 ስዓት ዩ.ኤስ.ኤም አልጀር ከ አል ማስሪ እና ቤርካኔ ከ ኤ.ኤስ ቪታ ክለብ ይገናኛሉ፡፡
በመጀመሪያው ጨዋታ ራዮን ስፖርትስ ከ ኢንየምባ 0 ለ 0 ሲለያዩ፤ ራጃ ካዛብላንካ ካራ ብራዛቪልን 2 ለ 1 ፤ ኤ.ኤስ ቪታ ቤርካኔን 3 ለ 1፤ አል ማስሪ ዩ.ኤስ.ኤም አልጀርን 1 ለ 0 ረትተዋል፡፡