loading
በኬንያ በዓለም አቀፍ ተቋሞች የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ያላቸውን ድጋፍ ገለፁ::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 በኬንያ በዓለም አቀፍ ተቋሞች የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ያላቸውን ድጋፍ ገለፁ::
በናይሮቢ በተባበሩት መንግስታትና በሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ማህበር (በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ በመደገፍ የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ መግለጻቸዉን በኬኒያ ከሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

የማህበሩ አባላት በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ ከመከሩ በኋላ ባወጡት የጋራ አቋም መንግስት የህዳሴ ግድብ በሚመለከት የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስከበር የወሰደውን አቋም እንደሚደግፉ ገልፀዋል፡፡

ከመንግስት በቀረበው ጥሪ መስረት የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ አባላቶቹ ገንዘብ ከመግዛት በተጨማሪ ከቀረቡ ፕሮጀክቶች ውስጥ አምስት አባላቱ በትምህርት ዘርፍ፣ በግብርና እና በገቢ ማስገኛ ከቀረቡ ብዙ ፕሮጀክቶች ውስጥ ከሌሎች ኢትዮጵያውንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ከህዝባችን ፍላጎት አኳያ ቅድሚያ መተግበር የሚገባቸውን ፕሮጀክቶች በመገምገም የተሳካ ስራ መስራታቸውም በውይይቱ ተጠቅሷል፡፡

በአጠቃላይ ማህበሩ የኢትዮጵያ መንግስት በህዳሴ ግድብ ውሀ አሞላልም ሆነ የአባይን ወንዝ ውሀ በፍትሀዊና እኩልነት ላይ በተመሰረተ የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገሮችን ትርጉም ባለው መልኩ ባለመጉዳት ለመጠቀምና የሀገራችን ጥቅም ለማስጠበቅ የወሰደውን አቋም የሚደግፉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለሀገራችን ያለውን ጥቅም በመገንዘብ ሁሉም አባላት ከዚህ ቀደም ቦንድ ግዥ የፈጸሙ ቢሆንም የህዳሴ ግድብ እንዲጠናቀቅ በሙያም ሆነ ቦንድ በመግዛት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *