በክልሉ ሰላምን ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የሶማሌ ክልል አስታወቀ
በክልሉ ሰላምን ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የሶማሌ ክልል አስታወቀ፡፤ የሶማሌ ክልል መንግሥት ከሰላም ወዳዱ ህዝብ ጋር በመሆን የክልሉን ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንደማይታገስና አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ማስታወቁን
የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።
በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በክልሉ ረብሻ፣ አለመረጋጋትና መንግስታዊ የኃላፊነት ቦታዎችን በኃይል ለመያዝ የተደረገ ሙከራ እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑንም የክልሉ መንግስት አመልክቷል። በአሁኑ ወቅት መላው የሶማሌ ክልል እንደ ወትሮው ሁሉ በሰላም እና መረጋጋት እንቅስቃሴ ላይ
መሆኑም ተገልጿል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በአንዳንድ ቦታዎች ፀረ ለውጥ የሆኑና በሙስና እንዲሁም በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ለውጥ አደናቃፊ አካላት ጋር በድብቅ ግንኙነት ሲያደርጉ ተደርሶባቸው ከመንግስት መዋቅር የወጡ ሀይሎች ሰላም ለማደፍረስ ያደረጉት ሙከራ ከሰላም ወዳዱ የክልሉ ህዝብ ጋር በመተባበር መክሸፉን
አስታውቋል።