በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሚከሰትን የደም አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ የምስራቅ ወለጋ ዞን አመራሮች ደም ለገሱ፡፡
የዞኑ ኮሚኒኬሽን ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ቀደም ሲል የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አገራዊ የደም አቅርቦት በመቀነሱ የልገሳ ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ ነዉ ፡፡
በልገሳ መረሓ ግብሩ የተገኙት የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አስመራ ኢጃራ በሰጡት አስተያየት፤ የኮሮናቫይረስ ከመግባቱ በፊት ሲቀርብ የነበረው ደም በመቀነሱ በችግር ጊዜ ሕዝብና አገርን የማሻገር ሃላፊነታችንን እንወጣለን ብለዋል።
ሌሎች የዞኑ አመራሮችም በደም እጥረት የሚቸገሩ ወገኖችን በመርዳታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው፣ ኅብረተሰቡ ከወሊድ ጋር በተያያዘና በአደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን የሚያጡ ወገኖችን መታደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በያዝነው አመት የኮሮና ወረርሺኝ ተጽኖ ቢያደርግም ከተለያዩ በጎ ፍቃደኞች አምስት ሺህ አንድ መቶ ዩኒት ደም መገኘቱን የገለጹት የነቀምቴ ደም ባንክ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ እንዳለም ገመዳ፣ ይህን መሰል የደም ልገሳ ጥረቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ የተፈጠረውን የደም እጥረት ከመቅረፉም በላይ ሌሎችን የየሚያነሳሳ ተግባር ነው ብለዋል።