loading
በኮፓ ኢጣሊያ ግማሽ ፍፃሜ ሚላን ከላትሲዮ በአቻ ውጤት ሲለያዩ ዛሬ ምሽት ሌላኛው ግጥሚያ ይደረጋል፡፡

በኮፓ ኢጣሊያ ግማሽ ፍፃሜ ሚላን ከላትሲዮ በአቻ ውጤት ሲለያዩ ዛሬ ምሽት ሌላኛው ግጥሚያ ይደረጋል፡፡

በጣሊያን ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ትናንት ምሽት ስታዲዮ ኦለምፒኮ ላይ ኤስ ሚላንን ያስተናገደው ላትሲዮ ያለግብ በአቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡

በድል ግስጋሴ ላይ ይገኝ የነበረው የጅናሮ ጋቱሶው ሚላን በትናንት ምሽቱ ግጥሚያ አሸንፈው ለመውጣት ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም፡፡

ለፍፃሜ ለመድረስ ግን ከሮማው ቡድን ይልቅ ሚዛኑ ወደ ሮዘነሪዎቹ ያዘነበለ ይመስላል፡፡ የመልሱ ግጥሚያም ከአንድ ወር በኋላ ሳን ሴሮ ላይ የሚከናወን ይሆናል፡፡

ዛሬ ሌላኛው የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ፊዮረንቲና በስታዲዮ አርቴሚዮ ፍራንች ላይ ከአታላንታ ቤርጋሞ ጋር ይፋለማል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ታላላቅ ክለቦቹን ሮማ እና ዩቬንቱስን ጥለው ለዚህ ጨዋታ የበቁ ሲሆን የሎምባርዲው ተወካይ አታላንታ አሮጊቷን 3 ለ 0 እንዲሁም ፊዮረንቲና ሮማን 7 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ድል በማድረግ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል፡፡

በሴሪ ኤው የደረጃ ሰንጠራዥ አታላንታዎች የተሻሉ ቢሆንም ባላቸው  ወቅታዊ አቋም የተነሳ የአሸናፊነቱ ግምት ወደ ፊዮረንቲና ያደላል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *