loading
በወልድያ እና ትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች ዕጣ ፈንታ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 09፣ 2014 በወልድያ እና ትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተወሰነ። በአሸባሪው የትህነግ ቡድን በተፈጠረው ችግር ምክንያት በወልድያና ትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በወልድያና ትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ለመመደብ የመመዝገቢያ ገጽ ተከፍቶ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ እና ምደባ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡ በዚህም በዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃቸውን በማዘጋጀት ከጥቅምት 09/2014 ዓ.ም ጀምሮ መመዝገብ እንደሚችሉ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *