loading
በወታደራዊ ስነ ምግባር ጥሰትና ኩብለላ ወንጀሎች ለተከሰሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ምህረት ማድረጉን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ያጸደቀውን የምህረት አዋጅ መሰረት በማድረግ በወታደራዊ የስነ ምግባር ጥሰት ተከሰው በማረሚያ ቤት የሚገኙና ቀደም ሲል ከሃገር የኮበለሉ የሰራዊት አባላት ምህረት ተደርጎላቸዋል ብለዋል።
የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀኔራል ኪዱ አለሙ፥ ለኢዜአ እንደገለጹት መንግስት በሃገር አቀፍ ደረጃ የጀመራቸውን የለውጥ እንቅስቃሴዎች ለማስቀጠል መከላከያ ሰራዊት ለውጡን በመደገፍ እየሰራ ነው።
የምህረት አዋጁ የሚመለከታቸው የሰራዊት አባላት ተቋሙ ባዘጋጃቸው አካባቢዎች ባሉ ጽህፈት ቤቶች በአካልም ሆነ በተዘጋጀ ፎርም ማመልከት እንደሚገባቸው እና ከአዲስ አበባ ውጭ ላሉ ታራሚዎች ባሉበት ክልል በተጠባባቂ የፍትህ ዳይሬክቶሬት ጽህፈት ቤት ሪፖርት ማድረግ የሚችሉ ሲሆን ፥ በወረዳና በዞን ላሉ ደግሞ በዞኑ በሚገኘው ጽህፈት ቤት ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት።
በዚህም ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ ጽህፈት ቤቱ ፎርሙን ማስሞላት እንደተጀመረ ጠቅሰው፥ በክልሎች ደግሞ ከነሃሴ አንድ ቀን ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ ሪፖርት ማድረግ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *