loading
በዋሽንግተን ሲካሄድ በቆየው የህዳሴ ግድብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ከ1 ሚሊዮን 1 መቶ ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20፣2013 በዋሽንግተን ሲካሄድ በቆየው የህዳሴ ግድብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ከ1 ሚሊዮን 1 መቶ ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ::
በዋሽንግተን የኢፌዲሪ ኤምባሲ ከበድር ኢትዮጵያ እና ከኡስታዝ ጀማል በሽር (የአባይ ንጉሶች መስራች) ጋር በመሆን በGoFundMe ሲያካሂድ የቆየው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የማጠናቀቂያና የምስጋና ምሽት በዋሽንግተን ዲ.ሲ. የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከናውኗል::

በወቅቱም አምባሳደር ፍጹም አረጋ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለግድቡ ግንባታ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ አስር ሺህ የአሜሪካን ዶላር ማሰባሰብ በመቻሉ የተሰማቸውን ደሰታ ገልጸዋል። ለአስተባባሪዎች እና ለለጋሾች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያን ወደ ብርሃን ለመውሰድ በዳያስፖራው የተደረገ ታሪካዊ ድጋፍ ተደርጎ ሲታወስ እንደሚኖርና ቀጣይም አንደሆነ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። በቀጣይ ለመለገስም ethiopiansforgerd.com ሊንክ በመጫን መለገስ የሚቻል መሆኑም ተገልጿል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *