loading
በዓለም አቀፍ ደረጃ እያጋጠመ ያለውን ፈተና እና የሚያመጣውን ተጽዕኖ ለመቋቋም አፍሪካውያን ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነታቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል ተባለ

አርትስ 05/03/2011
— ይህን ያሉት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳፋቂ መሀመት ዛሬ በተጀመረው የህብረቱ 20ኛ አስቸኳይ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው፡፡

እንደ ሊቀመንበሩ ገለፃ  በአሁኑ ወቅት ህብረቱ ባስቀመጠው የ2063 አጀንዳ  አንድ የጋራ ኢኮኖሚ ውህደት ለመፍጠር በየአቅጣጫው እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው፡፡

እንቅስቃሴውን በተቀናጀ መንገድ ለማስቀጠል ደግሞ የህብረቱን ማሻሻያ በፍጥነት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ  በአፋጣኝ የሚተገበር ነው ብለዋል፡፡

ሊቀመንበሩ የዛሬው የሚኒስትሮቹ  እና መጪው የመሪዎቹ ስብሰባ ዋና ትኩረትም የአፍሪካ ህብረት ማሻሻያ ብቻ ይሆናል ብለዋል፡፡

አፍሪካውያን በዓለም መድረክ በአንድ ድምፅ እንዲናገሩም እንዲደራደሩም ለማድረግ አህጉራዊ ተቋማት ላይ መስራት ይገባል ያሉት ሊቀመንበሩ; በተለይ የፓን አፍሪካ ፓርላማናየአፍሪካ ፍርድ ቤት ተጠናክረው  ወደ ስራ እንዲገቡ አባል ሀገራቱ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡።

ከዚህ ቀደም ከአውሮፓ ህብረት ጋር ተፈርሞ የነበረው የምጣኔ ሀብት ስምምነት ዳግም እንዲታደስና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ  መሰረቱን አድርጎ የሚያካሂደውን ድርድር አጠናክሮይቀጥላልም ብለዋል፡፡

የሩዋንዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባደረጉት ንግግር  ደግሞ ተቋማቱ የህብረቱን ማሻሻያ ተግባራዊ ከማድረግ በተጨማሪም  በዓለም አቀፍ ደረጃ ለአፍሪካ የሚደረገው እርዳታከመቼውም ጊዜ በላይ በዚህ ወቅት መቀነሱን እና አፍሪካውያን የራሳቸውን የፋይናንስ እጥረት በራሳቸው እንዲቀርፉ የሚለውን ማሻሻያ የተለየ ትኩረት እንዲታይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

20ኛው የአፍሪካ ህብረት የሚኒስትሮች አስቸኳይ ስብሰባ  እየተካሄደ ሲሆን በቀጣይም የህብረቱ የመሪዎች ስብሰባ ይጠበቃል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *