loading
በዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን 10 ሺህ ሰዎችን ቡና የማጠጣት ስነ ስርዓት ይከናወናል

በዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን 10 ሺህ ሰዎችን ቡና የማጠጣት ስነ ስርዓት ይከናወናል

አርትስ 26/02/2011

 በ13ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች  በዓል ኢትዮጵያን በአለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ ለማስፈር ነው 10 ሺህ ሰዎች በሚሳተፉበት የቡና መጠጣት ስነስርዓት እንደሚከናወን  የአዲስ አበባ ከተማአስተዳደር ያስታወቀው

በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበረውን  የብሄር ብሄረሰቦች በዓልን  አስመልክቶ ውይይት ተካሄዷል።

” አብረን ቡና እንጠጣ” በሚል መሪ ቃል  በአለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ የሚሰፍር ታላቅ የቡና መጠጣት ስነስርዓት እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን፥ በ5 ሰዓታት ከ10 ሺህ ሰዎች በላይ ሰዎች ይሳተፉበታልተብሏል።

የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በአል ኢትዮጵያዊነትን በሚያጎላ መንገድ ለማክበር መዘጋጀቱን  አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

በበአሉ ላይ ከየክልሉ ሺህ 200 እስከ 1 ሺህ 500 የሚደርሱ እንግዶች ወደ  አዲስ አበባ የሚገቡ ሲሆን፥ መዲናዋ እንግዶቿን ለመቀበል እየተዘጋጀች መሆኗን አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡ በበዓሉ ላይ የተለያዩ ስነስርዓቶችም ይከናወናሉ፡፡    

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *