loading
በደቡብ ሱዳን ተኩስ እና ጦርነት ቆሟል ተባለ

በደቡብ ሱዳን ተኩስ እና ጦርነት ቆሟል ተባለ

አርትስ 26/02/2011

ደቡብ ሱዳን ለ5 አመታት የነበረችበትን  የተኩስ እና ጦርነት ምዕራፍን መዝጋቷን እና የሰላም ስምምነት ልትፈርም መሆኑን  በአፍሪካ ህብረት እና በኢትዮጲያ የደቡብ ሱዳን ተጠሪ አምባሳደር ጀምስ ፒቲያምርገን ዛሬ በአዲስ አበባ በሰጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡

እንደ አምባሳደር ጀምስ ፒቲያምርን ገለፃ ከፈረንጆቹ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ደቡብ ሱዳን የተለያዩ የሰላም ስምምነቶችን ፈርማ ነበር ብለዋል፡፡

ነገር ግን ጦርነቱን ማስቆም አልቻለችም አሁን ግን  የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሰላም ጥሪን ተከትሎ አፍሪካዊያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው ያለማንም ጣልቃ ገብነት እንዲፈቱ በሚል  ማቻርን ጨምሮ ሌሎች ተቃዋሚዎችን ከፕሬዝዳንቱ ጋር ፊትለፊት እንዲወያዩ በማድረግ በጋራ የሚደረግ ስምምነት በመሆኑ ዋስትና ያለው ነው ብለዋል፡፡

አምባሳደር ጀምስ መቀመጫውን ኢትዮጲያ የነበረው እና አሁን ወደአሜሪካ የመሸገው ጀነራል ቶማስ ጅርሎን ጨምሮ ሌላ አንድ ተቃዋሚ ቡድን ሲቀር ሁሉም የደብብ ሱዳን ዜጎች የሰላም ስምምነቱን እንደተቀበሉ ገልፀዋል፡፡

የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ለ8 ወራት የሚቆይ የሽግግር መንግስት እና የሽግግር ጊዜ እንደሚኖር እና ከሁለት አመታት በኋላም ደቡብ ሱዳናዊያን በይፋ ምርጫ አድርገው መሪዎቻቸውን እንደሚመርጡ በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

አምባሳደሩ በጦርነቱ ምክንያት ከሃገሪቱ የወጡ እና በተለያዩ የቢዝነስ ሴክተሮች ተሰማርተው የነበሩ ኢትዮጲያዊያን እና የሌሎች ሃገር ዜጎች ወደቀድሞው ስራቸው እንዲመለሱ እና ሌሎችም የኢንቨስትመንት ዕቅድ ያላቸው አካላት በደቡብ ሱዳን እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *