loading
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሃገሩ በሚኖሩ ኢትዮጲያዊያን ዜጎች ላይ ጥቃት እንዳይፈፀም ከሃገሪቱ መንግስት ጋር እየሰራሁ ነው አለ፡፡

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሃገሩ በሚኖሩ ኢትዮጲያዊያን ዜጎች ላይ ጥቃት እንዳይፈፀም ከሃገሪቱ መንግስት ጋር እየሰራሁ ነው አለ፡፡

ባለፍው ሳምንት በሴዌቶ ከተማ በውጪ ሃገር ሰዎች የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የአንድ ኢትዮጲያዊ ህይወት ሲያልፍ ሌሎች ደግሞ ለአካል ጉዳት በመዳረጋቸው ኤምባሲው ለዜጎች ተገቢውን የመብት ጥበቃን እንዲደረግ ከደብብ አፍሪካው የውጪጉዳይ ሚኒስቴር እና የፀጥታ መዋቅር ጋር በትብብር እሰራለሁ ብሏል፡፡
የውጪጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት በድረ ገጹ እንደገለፀው የደብብ አፍሪካ መንግስት በስደት የሚኖሩ ዜጎችን ሰብአዊ መብትእንደሚያስጠብቅ ማረጋገጫ ሰጥቷል ብሏል፡፡
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙዜጎች ችግር ሲያጋጥማቸው በደቡብ አፍሪካ ለሚገኘው የኢትዮጲያ ኤምባሲ በስልክ ቁጥሮች 0123462110 እና 0123462947 ጥቆማ እንዲሰጡ ጠይቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *