በዲሞክራቲክ ኮንጎ የኢቦላ ህሙማን ቁጥር ጨምሯል ተባለ፡፡
በዲሞክራቲክ ኮንጎ የኢቦላ ህሙማን ቁጥር ጨምሯል ተባለ፡፡
በምስራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል በአንድ ቀን 14 በሽተኞች ሲገኙ ቫይረሱ በነሀሴ ወር ከተከሰተ ወዲህ ትልቁ ቁጥር ነው ተብሏል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው በሽታው የተከሰተው የፀጥታ ችግር ባለበት የሀገሪቱ ክፍል መሆኑ የጤና ባለሞያዎች ወደ ቦታው ተጎዘው በሽተኞችን እንዳይረዱ እንቅፋት ፈጥሯል፡፡
የዓለም የጤና ድርጅት በበኩሉ አሁን የታየው የህመምተኞች ቁጥር በጣም አስደንጋጭ እንደሆነ እና አስቸኳይ እርምጃ እንደሚያስፈልግ አስጠንቅቋል፡፡
እስካሁን በዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ጎንጎ በሰሜናዊ ኪቩ እና ኢቱሪ አካባቢዎች 439 ሰዎች በበሽታው ሳይሞቱ እንዳልቀሩ ይታመናል፡፡
የኢቦላ ቫይረስ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2013 እስከ 16 ባለው ጊዜ በምእራብ አፍሪካ ከ28 ሺህ በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ በሽታው ታይቷል ነው የተባለው፡፡
የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር በነሀሴ ወር በሽታው ከተከሰተ ጀምሮ ለ63 ሺህ ሰዎች ክትባት መስጠቱን ይፋ አድርጓል፡፡
ይሁን እንጂ አሁንም አለመረጋጋት ባለባቸው አካባቢዎች ከትባቱን ለመስጠት ትልቅ ችግር እንደተፈጠረባቸው ባለስልጣናቱ ተናግረዋል፡፡
ትርጉም በመንገሻ ዓለሙ