loading
በዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ የማራቶን ተወዳዳሪ አትሌቶች ተመርጠዋል፡፡

ለ17ኛ ጊዜ በዶሃ ኳታር እ.አ.አ. ከመስከረም 27 እስከ ጥቅምት 6/2019 ዓ. ም. ለሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ የማራቶን ቡድን አትሌቶችን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከነተጠባባቂዎቻቸው መርጧል፡፡

አትሌቶቹ በአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (IAAF) ዋና እና የወርቅ ደረጃ በተሰጣቸው ማራቶኖች እ.ኤ.አ ከመስከረም 2018 እስከ ሚያዚያ 2019 ድረስ ተወዳድረው ባስመዘገቡት የተሻለ ሰዓት ተመርጠዋል ብሏል ፌዴሬሽኑ ፡፡

በዚህ መሰረት፡-

በወንዶች፣

  1. አትሌት ሞስነት ገረመው፤ 2019፣ ለንደን፣ 2፡02.55
  2. አትሌት ሙሌ ዋሲሁን፤ 2019፣ ለንደን፣ 2፡03.16
  3. አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ፤ 2018፣ ኒው ዮርክ፣ 2፡05.59
  4. አትሌት ሹራ ኪጣታ፤ 2019፣ ለንደን፣ 2፡05.01 ተጠባባቂ፣
  5. አትሌት ብርሃኑ ለገሰ፤ 2019፣ ቶኪዮ፣ 2፡04.48 ተጠባባቂ፣
  6. አትሌት ታምራት ቶላ፤ 2018፣ ዱባይ፣ 2፡04.06 ተጠባባቂ፣

በሴቶች፣

  1. አትሌት ሩቲ አጋ፤ 2018፣ በርሊን፣ 2፡18.34
  2. አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ፤ 2019፣ ዱባይ፣ 2፡17.41
  3. አትሌት ሮዛ ደረጀ፤ 2018፣ ዱባይ፣ 2፡19.17
  4. አትሌት ሹሬ ደምሴ፤ 2019፣ ቶኪዮ፣ 2፡21.05 ተጠባባቂ፣
  5. አትሌት ሄለን ቶላ፤ 2019፣ ቶኪዮ፣ 2፡21.01 ተጠባባቂ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባገኘነው መረጃ፤ የሰዓት ልዩነት የሚታየው በአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (IAAF) ደረጃ አሰጣጥ መሰረት የማራቶኖቹ ደረጃ ስለሚለያይ መሆኑን እና በምርጫው ቅሬታ ያለው አትሌት ካለ ቅሬታውን በጽሁፍ ለፌዴሬሽኑ እስከሚቀጥለው ሳምንት ግንቦት 27/2011 ዓ. ም ድረስ ማቅረብ ይችላል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *