loading
በዶክተር ወርቅነህ የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ወደ ጅቡቲ ተጓዘ፡፡

በዶክተር ወርቅነህ የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ወደ ጅቡቲ ተጓዘ፡፡

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ዶከተር ወርቅነህ ገበየሁ የተመራ ከፍተኛ የአገራችን የልኡካን ቡድን በዛሬው እለት  በ15ኛው የኢትዮ-ጂቡቲ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ  ላይ ለመሳተፍ ወደ ጅቡቲ መጓዙን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

የልኡካን ቡድኑ ከተለያዩ መስሪያ ቤቶችና ተቋማት የተውጣጣ ከአስር በላይ ሚኒስትሮችንና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ያከተተ ነው።

ኢትዮጵያና ጅቡቲ ዘርፈ ብዙ የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፤ የጅቡቲ ወደብ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ለኢትዮጵያ ዋነኛ የወጪና የገቢ ንግድ መስመር ሆኖ ማገልገሉ ግንኙነቱ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው የራሱን ድርሻ አበርክቷል።

ሁለቱ አገሮች በመሰረተ ልማት የተሳሰሩ ከመሆናቸውም በላይ የጋራ ኮሚሽን አቋቁመው ግንኙነታቸውን በየጊዜው እየገመገሙ ይገኛሉ።

የጋራ ኮሚሽን መቋቋሙ በትብብር ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት አስችሏል።

በአሁኑ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ወቅት በዋነኛነት በትራንስፖርት፣ በወደብ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በጉምሩክና በንግድ ጉዳዮች ትኩረት ተደርጎ ውይይት ይደረጋል።

የጋራ ኮሚሽኑ በእነዚህ ዘርፎች የሁለቱ አገሮች የትብብር ግንኙነት እንዲጠናከር ይመክራል። ባጋጠሙ ችግሮች ላይ የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *