loading
በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ምክንያት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከአሜሪካ አልፎ ዓለም አቀፍ ይዘት እየተላበሰ ነው ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2012 በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ምክንያት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከአሜሪካ አልፎ ዓለም አቀፍ ይዘት እየተላበሰ ነው ተባለ::
አሁን ላይ የጥቁሮች ህይዎት ያሳስበናል የሚለው ተቃውሞ ከአሜሪካ ከተሞች አልፎ በእግሊዝ፣ በጀርመን በኒው ውዚ ላንድ እና በሌሎች ሀገራትም እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በቅርቡ በፖሊስ መኮንን የተገደለው ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ጉዳይ በኮሮናቫይረስ ለምትታመሰው አሜሪካ ሌላ ራስ ምታት ሆኖባታል፡፡
ቢዝነስ ኢንሳይደር እንደዘገበው ትላልቅ የአሜሪካ ኩባንያዎች የፍሎይድን ግድያ በመቃወም ለስድስተኛ ቀናት አደባባይ የወጡትን ሰልፈኞች እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡ ተቃውሞውን ከደገፉት ኩባንያዎች መካከል ናይክ፣ ቱዊተር፣ ሲቲ ግሩፕ እና ኔት ፍሊክስ ዋነኞችናቸው ተብሏል፡፡

ፍሎይድ የፖለስ መኮንኑ አንገቱን ተጭኖ ይዞ ትንፋሽ ሲያሳጣው እያጣጣረ የተናገረው “መተንፈስ አልቻልኩም” የሚለው ቃል የሰልፈኞቹ ዋነኛ የተቃውሞ መፈክር ሆኗል፡፡ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ጥላው የነበረውን የእንቅስቃሴ እገዳ ማንሳት የጀመረችው አሜሪካም ረብሸው ተባብሶ በመቀጠሉ ምክንያት 40 በሚሆኑ ከተሞች ላይ የሰዓት እላፊ አዋጅ ደንግጋለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *