loading
በጉራጌ ዞን በድምቀት የሚከበሩ የሀይማኖትና ባህላዊ በዓላት ህዝቡ ባሉበት እንዲያከብሩ መወሰኑን የዞኑ ግብረ ሃይል አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ሐምሌ15፣ 2012 በጉራጌ ዞን በድምቀት የሚከበሩ የሀይማኖትና ባህላዊ በዓላት ህዝቡ ባሉበት እንዲያከብሩ መወሰኑን የዞኑ ግብረ ሃይል አስታወቀ፡፡በጉራጌ ዞን ኮቪድ መከላከል እና መቆጣጠር ግብረ ሃይል የአረፋ በአልን አስመልክቶ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ፤የኮቪድ 19 በሀገራችን ከተከሰተ ጀምሮ ወረርሽኙን በመከላከል ፤ በመቆጣጠር ግብረሃይሉ ጥረት እያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ግብረ ሃይሉ በሌላ መልኩ ከአርሶ አደር ከመንግስት ሰራተኛ ከባለሃብትና ሌሎች በጎአድራጊ ድርጅቶች እና ከመንግስት በአይነት በጥሬ ገንዘብ ከ 50 ሚሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ ለዚሁ ስራ እንዲዉል እተደረገ ይገኛል ፡፡አሁን እንደዞናችን ከፊትለፊት አረፋና መስቀል በዓለት አሉ አነዚህ በዓላት ሃማኖታዊና ባህላዊ ይዘት ያላቸዉ በመሆኑ በርካታ የዞኑ ተወላጆች በዓሉን ለማክበር ወደ ሃገርቤት ይገቡ ነበር ዘንድሮ ግን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ያንን ማድረግ ሳይቻል ቀርቷል ብለዋል፡፡ግብረ ሃይሉ የዘንድሮ የዓረፋ በአል አሁን ከገጠመን አጠቃላይ ችግርና ፈተና አንጻር የሃይማኖት አባቶች ሽማግሌዎች ወላጆችን ምክር በማዳመጥ ሁሉም ቤለበት እንዲያከበር መወሰኑን የዞኑ ግብረ ሃይል ለአርትስ በላከዉ መግለጫ አስታዉቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *