loading
በጋዛ የሚገኙ አንድ ሚሊዮን ፍልስጤማዊያን ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 በጋዛ የሚገኙ አንድ ሚሊዮን ፍልስጤማዊያን ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል ተባለ፡፡
እስራኤል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለፍልስጤም ስደተኞች የሚልከውን ድጋፍ እንዳይደርስ በማገዷ በጋዛ የሚኖሩ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጤማዊያን ለምግብ እጥረት መጋለጣቸው ነው የተነገረው፡፡ አሜሪካ ለፍልስጤም ስደተኞች የሚሆን በዓመት 360 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን እርዳታ ማቆሟ ደግሞ ጉዳቱን ያባባሰው ሌላኛው ጉዳይ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ የምግብ እጥረቱና በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ስጋትን የፈጠረው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መባባስ ችግሩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል፡፡ እስራኤል ከፈረንጆቹ 2006 ወዲህ በጋዛ ትፈጽመዋለች በተባለው የድንበር መዝጋት ድርጊት ድህነትና ስራ አጥነት በከፍተኛ ሁኔታ መበራከቱ ነው የተነገረው፡፡ በፈረንጆቹ ጁን 20 የተከበረው የዓለም ስደተኞች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች አስከፊ ህይወት አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ የተሰራበት መሆኑን ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *