በጣሊያን ኮፓ አጣሊያ ኤስ ሚላን ከናፖሊ ተጠባቂ ጨዋታቸውን ዛሬ ምሽት ያደርጋሉ
በጣሊያን ኮፓ አጣሊያ ኤስ ሚላን ከናፖሊ ተጠባቂ ጨዋታቸውን ዛሬ ምሽት ያደርጋሉ
ይህ የኮፓ ኢጣሊያ የሩብ ፍፃሜ የምሽት ተጠባቂ ግጥሚያ በጁሴፔ ሜዛ የሚከናወን ሲሆን ምሽት 4፡45 ሲል ይጀመራል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች ከሶስት ቀናት በፊት በዚሁ ሜዳ በሴሪ ኤው ተገናኝተው ያለግብ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ሮዘነሪዎቹ የሚያሳዩትን ወጣ ገባ አቋም፤ ደጋፊው በሚፈልገው መንገድ ማስተካከል የተሳናቸው ሲሆን የዋንጫ ጥማቸውን ለመቁረጥ የዛሬው ጨዋታ ወሳኝ ነው፡፡
ከኤስ ሚላን ጋር የኮፓ ኢጣሊያን ዋንጫ ማሳካት የቻሉት የናፖሊው አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲ ግን ለጅናሮ ጋቱሶ ቡድን በቀላሉ እጅ ይሰጣሉ ብሎ መጠበቅ ያስቸግራል፡፡
አዲሱ የሚላን ፈራሚ ክሪስቶቭ ፒያቴክ የመጀመሪያ ሙሉ ጨዋታውን ያከናውናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ተጫዋቹ በሚላን ማሊያ የመጀመሪያ ጨዋታውን በሴሪ ኤው ግጥሚያ ተቀይሮ መግባቱ ይታወሳል፡፡
ክሪስቲያን ዛፓታ፣ ማቲያ ካልዳራ፣ ሉካስ ቢግሊያ እና ፔፔ ሬና ደግሞ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጭ ናቸው፡፡
ከቭላድ ችሪቼስ ውጭ የተጫዋች ጉዳት የሌለባቸው ናፖሊዎች፤ የቡድኑ የመጀመሪያ ተሰላፊ ተጫዋቾች በካርሌቶ በኩል ዕረፍት ሊሰጣቸው እንደሚችል ተነግሯል፡፡
በሌሎች የሩብ ፍፃሜ ፍልያዎች ነገ ፊዮረንቲና ከ ሮማ እንዲሁም አታላንታ ከ ዩቬንቱስ ይገናኛሉ፡፡ ኢንተር ሚላን ደግሞ ሀሙስ ሳንሲሮ ላይ ላትሲዮን ያስተናግዳል፡፡