loading
በጣና ሀይቅ የአሳ ሀብት መመናመን ተጠያቂዉ የክልሉ መንግስት ነዉ ተባለ

አርትስ 4/1/2011
ይህንን ያሉት በአሳ ሀብትላይ ላለፉት 25 ዓመታት ምርምር ያደረጉትና በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የአሳ ሀብት ተመራማሪ ዶክተር እሸቴ ደጀኔ ናቸዉ፡፡
ዶክተሩ ለአማራ መገናኛ ብዘሁሃን መንግስት የአሳ ሀብቱን ለመጠበቅ የወጡ መመርያዎችን ተግባራዊ ባለማድረጉ የዓሳ ሀብቱ ተመኗል ለዚህም መንግስት ተጠያቂ ነዉ ብለዋል ፡፡
በለሞያው በጣና ሀይቅ ላይ ለባለፉት 25 አመታት ጥናትና ምርምር ያደረጉ ሲሆን ፤ጣና ከሌሎች አካባቢዎች የማይገኙ የተለየ ዝርያ ያላቸው አሳዎችን ጨምሮ እስከ 15ሺህ ቶን ምርት በዓመት ይሰጥ እንደነበር በምርምራቸው አስታውሰዋል፡፡
ባሳለፍነው ዓመት በተደረገ ጥናት የጣና ሀይቅ አቅሙ ተዳክሞ 7ሺህ ቶን አሳ የማምረት አቅም ብቻ እንዳለው ታውቋል፡፡
ዶክተር እሸቴ በፈረንጆቹ 2003 የክልሉ መንግስት የአሳ ሀብት አጠቃቀምን በተመለከተ፤ በ2015 ደግሞ የጣና ሀይቅ አያያዝ ላይ ያተኮሩ አዋጆችን ያወጣ ቢሆንም ተግባራዊ ሳያደርገዉ መቅረቱን አስታዉሰዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *