loading
በጥቂት ዓመታት በመላው ኢትዮጵያ 20 ቢሊዮን ችግኞች  እንደሚተከሉ  ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ ተናገሩ፡፡

በጥቂት ዓመታት በመላው ኢትዮጵያ 20 ቢሊዮን ችግኞች  እንደሚተከሉ  ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ ተናገሩ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት፣ የዚህን ዓመት የ አረንጓዴ አሻራ   የችግኝ ተከላ ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ የግብርና ሚኒስቴር ማብራሪያ አቅርቧል፡፡የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴው አባላት፣ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት፣ የክልል ፕሬዚደንቶች፣ ሕዝቡን የማነሳሳት ሥራን የሚከውኑ ተጽዕኖ አሳዳሪ ግለሰቦችን ጨምሮ ዐበይት ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል፡፡ባለፈው የችግኝ ተከላ ወቅት ዜጎች በከፍተኛ ሁኔታ ተነሣሥተዋል፣ ንቃት የተሞላ የመንግሥት አመራር ታይቷል፣ የተቋማት ትብብር እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ተስተውሏል፡፡ እነዚህን መልካም ተሞክሮዎች ማስፋት እንደሚያስፈልግ በውይይቱ ተነሥቷል፡፡የዚህ ዓመት ግብ 5 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ሲሆን፣ ለዚህ የሚያበቃ ብዛት ያለው ችግኘ እንዲፈላ ቅድመ ዝግጅት ሲካሄድ  መቆየቱም በዉይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጅማሮዎችን የማስቀጠልን ጠቃሚነት አንሥተው፣ አረንጓዴ አሻራ   በመጪዎቹ ጥቂት ዓመታት በመላው ኢትዮጵያ 20 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡በተጨማሪም፣ አዲስ አበባን የማስዋብ፣ የከተማ ቱሪዝምን የማስፋፋትና ለመኖር ምቹ የሆነች ከተማን መፍጠር ዓላማው የሆነው ፕሮጀክት ያካተታቸውን የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ገልጸዋል፡፡መረጃዉን ያገኘነዉ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ነዉ፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *