በፈረንሳይ የኮሮናቫይረስ ስርጭት በአንድ ሳምንት ውስጥ በ40 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተባለ::
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 በፈረንሳይ የኮሮናቫይረስ ስርጭት በአንድ ሳምንት ውስጥ በ40 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተባለ::በመላው አውሮፓ እንደ አዲስ እየተስፋፋ የመጣው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ፈረንሳይንም ከፍተኛ ስጋት ለይ ጥሏታል፡፡
የፈረንሳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂያን ካንቴክስ በሰጡት መግለጫ ችግሩ በጠቅላላው አውሮፓም በሀገራችንም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል፡፡የወረርሽኙ ስርጭት ያሳሰባት ፈረንሳይ በተመረጡ አካባቢዎች የሰአት እላፊ ገደቦችን ለመጣል ተገዳለች፡፡ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው በፈረንሳይ በየ 15 ቀኑ የቫይረሱ ስርጭት የመባባስ አዝማሚያ እያሳየ ይገኛል፡፡
የሀገሪቱ ባለስልጣናት ሁሉም ፈረንሳዊያን በሚንቀሳቀሱበት ስፍራ ሁሉ የፊት መሸፈኛ ጭንብል ማድረግና ሌሎች የጥንቃቄ መንገዶችን መከተልን እንዳይዘነጉ አስጠንቅቀዋል፡፡ፈረንሳይ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙባት ሲሆን በበሽታው ምክንያት ምክንያት ከ34 ሽህ በላይ ሰዎች ህይዎታቸው አልፏል፡፡
አሁን ላይ በአብዛኛው የአውሮፓ ክፍል ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ስርጭት በፍጥነት እየተስፋፋ ከመሆኑ ጋር ተያይዙ ብዙዎቹ ሀገራት የእንቅስቃሴ እቀባዎችን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ፡፡