loading
በፓኪስታንዋ ፔሻወር ከተማ በትምህርት ቤት ዉስጥ በደረሰ ፍንዳታ 7 ሰዎች ሞቱ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013 በፓኪስታንዋ ፔሻወር ከተማ በትምህርት ቤት ዉስጥ በደረሰ ፍንዳታ 7 ሰዎች ሞቱ::ከሞቱት መካከልም አራቱ ህጻናት ናቸዉ ተብሏል::በቢሲ እንደዘገባዉ ፖሊስ በሀይማኖታዊ ትምህርትቤቱ በደረሰዉ ጥቃትም ከ50 በላይ ሰዎች መቁሰላቸዉን ገልጿል::

የሆስፒታል ምንጮች እንደገለጹት ወደ ሆስፒታሉ ቆስለዉ እና ህይወታቸዉ አልፎ የመጡ ሰዎች በፍንዳታ የተጎድ እንደሆኑ አረጋግጧል በጥቃቱ ህይወታቸዉ ካለፉት አራት ህጻናት በተጨማሪ ሌሎቹ ከ20 አስከ 30 የእድሜ ክልል ዉስጥ የሚሆኑ ወጣቶች መሆናቸዉ ታዉቋል::

ከቆሰሉት መካከልም 12 ቱ ከ 4ዓመት እስከ 13 አመት የእድሜ ክልል ዉስጥ እንደሆኑ ዘገባዉ ጠቅሷል::የፔሻወር ከተማ በአፍጋኒስታን ድንበር አካባቢ የሚገኝ ከተማ ሲሆን፡ በታሊባን ተደጋጋሚ አደጋ የሚደርስብት አካባቢ እንደሆነ ተገልጿልከ 6 ዓመት በፊትም በፔሻወር አንድ መሳሪያ የታጠቀ ሰዉ በትምህርት ቤት ባደረሰዉ ጥቃት ከ150 በላይ ሰዎች መገደላቸዉ ይታወሳል፡፡ከነዚህ መካክልም ብዙዎች ህጻናት እንደነበሩ ዘገባዉ አስታዉሷል::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *