loading
በ2ኛው የዓለም ጦርነት የተሳተፉ የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች ከ75 ዓመት በኋላ ውቅና አገኙ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 20፣ 2013 በ2ኛው የዓለም ጦርነት የተሳተፉ የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች ከ75 ዓመት በኋላ ውቅና አገኙ:: ወደ 80,000 የሚሆኑ ጥቁር ደቡብ አፍሪቃውያን እንደ የወታደራዊ ጓድ አካል ሆነው በጦርነቱ ቢሳተፉም ከነጭ ወታደሮች ያነሱ ተደርገው የእነሱ አስተዋፅዖ ሳይነገር ተዳፍኖ ቀርቶ ነበር፡፡ አሁን ግን በኮመንዌልዝ በኩል በተቋቋመው ኮሚሽን በወቅቱ ለተዋጉትና ለሞቱት እንዲሁም አሁንም በህይዎት ለሚገኙ ወታደሮች የመታሰቢያ ሂደት ከጀመረ በኋላ እውቅና እየተሰጣቸው ነው፡፡

በዚህም ሳቢያ 800 ሺህ የሚሆኑ በሁሌኛው ዓለም ጦርነት የተሳተፉ ጥቁር የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች ናቸው እውቅና የተሰጣቸው፡፡ አሁን በህይዎት የሚገኙት የ106 ዓመቱ አዛውንት የያኔው ተዋጊ ሲሞን ማላንጋ በጣሊያን የየጦር እስረኞች ጠባቂ ሆነው ሲያገለግሉ እንደነበርና ያለምንም ምስጋና እንደተመለሱ ይናገራሉ፡፡

አሁን ላይ እንዚህን በወቅቱ የተናቁ ወታደሮች እውቅና እዲያገኙና እንዲታሰቡ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ምንም እንኳ ቢዘገይም በርካቶች እያደነቁት ነው፡፡
በመቃብር ስፍራዎች ውስጥ ጥቁር ወታደሮች ከነጭ ጓዶቻቸው ጎን እንዲያርፉ አልተፈቀደላቸውም ነበር ተብሏል፡፡ ሲሞን ማላንጋም ቢሆኑ ህይዎታቸው ሳይልፍ ቢያንስ ባለቻቸው ቀሪ የሰሩት ጀግንነት እውቅና ማግኘቱ በደስታ አስደንሷቸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *