loading
በ7 ቀናት ውስጥ 2 በመቶ የዩክሬን ዜጎች ተሰደዋል- ተ.መ.ድ በጦርነቱ ሳቢያ በ7 ቀናት ውስጥ 1 ሚሊዮን ዩክሬናዊያን ወደ ጎረበት ሀገራት መሰደዳቸው ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 በ7 ቀናት ውስጥ 2 በመቶ የዩክሬን ዜጎች ተሰደዋል- ተ.መ.ድ በጦርነቱ ሳቢያ በ7 ቀናት ውስጥ 1 ሚሊዮን ዩክሬናዊያን ወደ ጎረበት ሀገራት መሰደዳቸው ተሰማ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ የዩክሬናዊያን ስደት በፍጥነቱ የክፍለ ዘመኑን ክብረ ወሰን ሊይይዝ እንደሚችል ያሳያል ብሏል፡፡


በቅርብ ቀናት ውስጥ ይህ ቁጥር ወደ 4 ሚሊዮን ከፍ ሊል እንደሚችል ተንብዮ የነበረው ኮሚሽኑ ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለ ግን ቁጥሩ ከተጠበቀው በላይ እንደሚሆን ስጋቱን ገልጿል በተመሳሳይ ችግር በዓለማችን ከፍተኛ ህዝብ በተሰደደባት ሶሪያ 1 ሚሊዮን ሰዎች ከሶሪያ ለመውጣት
3 ወር መውሰዱንም ተቋሙ በንጽጽር አቅርቧል፡፡


የሩሲያ ወታደሮች በዩክሬን ጦርነት በከፈቱባት የመጀመሪያዋ ቀን 82 ሺህ ሰዎች የተሰደዱ ሲሆን ከዚያ ወዲህ ባለው ጊዜ በየቀኑ በአማካይ 117 ሺህ ዩክሬናዊያን ሀገራቸውን ለቀው እንደሚወጡ ኮሚሽኑ አብራርቷል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት እስካሁን የዩክሬን ጎረቤቶች በራቸውን ክፍት አድርገው ስደተኞቹን በመቀበል ላደረጉት ትብብር አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2020 በተደረገው ቆጠራ 44 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ዩክሬን በአሁኑ ጊዜ 2 በመቶ የሚሆኑት ዜጎቿ ድንበር አቋርጠው በመሰደድ ላይ መሆናቸው ተነግሯል፡፡ የዩክሬን የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ተቋምን ጠቅሶ ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው እስካሁን በጦርነቱ ሳቢያ 2 ሺህ ያህል ንጹሃን ዜጎቸ ተገድለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *