loading
ቢሮው ህግን ተላልፈው በከተማ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ እስከ 6 ሺህ ብር እንደሚያስቀጣ አስታወቀ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 ቢሮው ህግን ተላልፈው በከተማ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ እስከ 6 ሺህ ብር እንደሚያስቀጣ አስታወቀ:: ሕግን ተላልፈው በከተማ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርከሪዎች ላይ እስከ 6 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት መጣሉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅና አደጋን ለመቀነስ ከቀኑ 10 ሰዓት እስከ ምሸት 2 ሰዓት የወጣውን የሰዓት እገዳ መመሪያ ገቢራዊ እንዲያደርጉም አሳስቧል።ቢሮው ለኢዜአ በላከው መግለጫ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ ከባድ ተሽከርከሪዎች ከቀኑ 10 ሰዓትእስከ ምሽት 2 ሰዓት ወደከተማዋ ማስገባትና ማንቀሳቀስ በመመሪያ መከልከሉን አስታውሶ፤ ሆኖም ግን ይህን ድንጋጌ የሚተላለፉ ተሽከርካሪዎች መኖራቸውን ገልጿል።

በዚህም የመጫን አቅማቸው ከ2 ነጥብ 5 ቶን በላይ የሆኑ ተሽከርካሪዎች እንደጥፋቱ ክብደትና ድግግሞሽ ከብር 500 እስከ 6 ሺህ እንደሚቀጡ፣ ከ1 እስከ 3 ወር የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድንም እንደሚያግድ ገልጿል።በተከለከለው ሰዓት ካለመንጃ ፈቃድ ተሽከርካሪን ወደ ከተማዋ ማስገባት፣ ማንቀሳቀስና በዋና መንገድ ላይ ጭነት መጫንና ማውረድ በመጀመሪያ ድርጊት 1 ሺህ ብር፤ በሁለተኛው ጥፋት ደግሞ 2 ሺህ ብር ያስቀጣል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *