loading
 ባለስልጣኑ  ሰባት መንገዶችን በአስፓልት ደረጃ ለመገንባት የሚያስችል የውል ስምምነት አካሔደ።

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2012 ባለስልጣኑ  ሰባት መንገዶችን በአስፓልት ደረጃ ለመገንባት የሚያስችል የውል ስምምነት አካሔደ።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከ11 ነጥብ ስድስት ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ ሰባት መንገዶችን በአስፓልት ደረጃ ለመገንባት የሚያስችል የውል ስምምነት ማከሄዱን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡የውል ስምምነት የተፈረመላቸው ሰባት መንገዶች በጥቅሉ ከ500 ኪ.ሜ በላይ ርዝመት አላቸው።ለግንባታቸው የሚውለው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግሥት የሚሸፈን መሆኑ ተገልጿል።

መንገዶቹ ከደብረ ብርሃን-ደነባ-ለሚ መገንጠያ እና ጅሁር-ደነባ፣ ከፊቅ-ሰገግ-ገርቦ ደነን እንዲሁም ዮአሌ-ደነን፣ ከሁምቦ-ጠበላ-ዐባያ፣ ዳዬ-ግርጃ-ክብረ መንግሥት እና ከመለያ-መጆ መገንጠያ፣ ከጅግጅጋ-ገለለሽ-ደጋሀምዶ-ሰገግ፣ ከሀወላቱላ-ወተርአራሳ-ያዩ-ውራቼ እና ከዛላአምበሳ-አሊቴና-መረዋ-ዕዳጋ ሐሙስ ናቸው።መንገዶቹን ለመገንባት ከባለሥልጣኑ ጋር የውል ስምምነት ያደረጉት ተቋራጮች ስድስቱ አገር በቀል ሲሆኑ፣ አንዱ የውጭ ተቋራጭ መሆኑ ታውቋል።የመንገዶቹንም ግንባታ ለማጠናቀቀም ከሦስት እስከ አራት ዓመታት እንደሚወስድ ተጠቅሷል።በአሁኑ ሰዓት መንገዶቹ በጠጠር ደረጃ የሚገኙ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በአስፓልት ደረጃ ከተማ ውስጥ አሥር ሜትር እንዲሁም በገጠር ሰባት ሜትር ስፋት ይኖራቸዋል ተብሏል።በመሆኑም መንገዶቹ በታቀደላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ ኅብረተሰቡ ከወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ ለሚነሡ ጉዳዮች አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጠይቋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *