loading
ባላመንበት ጦርነት የገባነው ድብደባ በዝቶብን ተሰቃይተን ነው- የሕወሓት ምርኮኞች ባላመንበት ጦርነት የገባነው እምቢ በማለታችን ድብደባና አፈና በዝቶብን ተሰቃይተን ነው::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2013 ባላመንበት ጦርነት የገባነው ድብደባ በዝቶብን ተሰቃይተን ነው- የሕወሓት ምርኮኞች ባላመንበት ጦርነት የገባነው እምቢ በማለታችን ድብደባና አፈና በዝቶብን ተሰቃይተን ነው በአፋር ግንባር ተሰልፈው የነበሩ የሕወሓት ምርኮኞች ተናገሩ። ካልአይ መምበረ በፈንቲ – ረሱ ግንባር በተካሄደው ውግያ ቆስሎ የተማረከ ሲሆን ከመቀሌ ከተማ ድንገት ታፍኖ ከታሰረ በኋላ የሦስት ቀናት ስልጠና ከተሰጣቸው መካከል አንዱ በመሆን ወደ ግንባር
መምጣቱን ተናግሯል።

በግንባር ሲገባም እሱን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ወጣቶች ከመከላከያ ቀምተን እንሰጣችኋለን ብለዋቸው ያለመሳሪያ ወደ ጦርነት እንዳስገቧቸው ጠቅሶ ፤ በዚህ ሂደት ለማምለጥ ሲሞክርም ተመቶ መያዙን ነው የገለጸው። ወደ ጦርነት የገባነው እምቢ በማለታችን ድብደባ በዝቶብን ተሰቃይተን ነው ብሏል። ሌላው ምርኮኛ አንገሶም ገብረስላሴ በመቀሌ ከተማ በአሽከርካሪነት ከሚሠራበት በግድ ታፍኖ በመወሰድ መሳሪያ የመፍታትና መግጠም ስልጠና ብቻ ተሰጥቶት ወደ ጦርነት ተገዶ መግባቱን ተናግሯል።

ውጊያው እንደተጀመረም አብረውት የነበሩ በርካታ ሰዎች ሞተውና ቁስለኛ ሆነው ሲያይ ደንግጦ ህይወቱን ለማትረፍ ለመሸሽ ሲሞክር ተመቶ እንደተያዘ ነው ያስረዳው። የመከላከያ ሠራዊትና የአፋር ልዩ ኀይል ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ በሰብዓዊነትና ወገናዊነት በተሞላበት መልኩ እንክብካቤና ድጋፍ እያደረጉላቸው መሆኑን ጠቅሶ ለዚህም ምስጋና አቅርቧል። ምንም የማያውቁ ሲቪሎችና ታዳጊ ሕጻናት በግፍ ወደ ጦርነት እየተማገዱ በመሞት ላይ ስለሚገኙ የትግራይ ሕዝብ ከዚህ በኋላ ለአሸባሪው መጠቀሚያ መሆን አይገባውም ብሏል። የትግራይ ሕዝብ ለአሸባሪዎቹ የስልጣን መጠቀሚያ መሳሪያ ከመሆን በመቆጠብ ቡድኑን በቃህ
ሊለው እንደሚገባም ወጣቶቹ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *