loading
ብራዚል በኮሮናቫይረስ ሳቢያ የሟች ዜጎቿ ቁጥር በዓለም ሁለተኛ ደረጃ እንድትቀመጥ አድርጓታል

አዲስ አበባ፣ሰኔ 7፣2012 ብራዚል በኮሮናቫይረስ ሳቢያ የሟች ዜጎቿ ቁጥር በዓለም ሁለተኛ ደረጃ እንድትቀመጥ አድርጓታል:: ደቡብ አሜሪካዊቷ ሃገር ብራዚል ዓርብ ዕለት በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ዜጎች ቁጥርን ከፍ በከፍተኛ መጠን የመዘገበች መሆኑን ተከትሎ ሁለተኛ ደረጃን ከአውሮፓዊቷ እንግሊዝ ተረክባለች፡፡ ይሄንን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት የሀገሪቱ የጤና ስርዓት ትልቅ ጫና ውስጥ ይገኛል ብሏል፡፡የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ዓርብ ዕለት የ24 ሰዓት ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርግ አዲስ በበሽታው የተያዙ ዜጎች ቁጥር 25,982 እንደሆነ እና 909 የሞት መጠን የተመዘገበ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ከ41 ሺ 900 በላይ ሆኗል፡፡ በቫይረሱ የተጠቁት ዜጎች ቁጥር ደግሞ ከ829ሺ በላይ ሆኗል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ አደጋ ዋና ባለሙያ የሆኑት ማይክ ርያን በብራዚል ያለው ሁኔታ “አሁንም አሳሳቢ ነው” ያሉ ቢሆንም በሀገሪቱ በአብዛኛዎቹ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የፅኑ ህሙማን የአልጋ አቅርቦት መጠን ከ80 በመቶ በታች መሆኑን አምነዋል ሲል አልጄዚራ ዘግቧል፡፡ርያን በጄኔቫ ባደረጉት ንግግር ላይ በአጠቃላይ ሲታይ የጤና ስርዓቱ በብራዚል ውስጥ አሁንም በሁለት እግሩ የቆመ አለመሆኑን የጠቆሙ ሲሆን ቀጣይነት ያለው ከፍተኛ የሆነ ኬዝ ወደፊት እንደሚታይ ተናግረዋል፡፡

በሀገሪቱ በቫይረሱ የሚጠቁ እና የሚሞቱት ዜጎች ቁጥር ከፍ እያለ ቢሆንም በብራዚሉ ፕሬዚዳንት ዣዬር ቦልሶናሮ እና ተከታዮቻቸው እያሳደሩት ባለው ጫና ሀገሪቱ የጣለቻቸውን ገደቦችን እያላላች ሲሆን የቢዝነስ ተቋማትንም እየከፈተች ትገኛለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *