loading
ብራዚል ኮሮናቫይረስ ከቁጥጥሬ ውጭ አይደለም ብትልም በቀን ውስጥ የሚመዘገበው የሟችና የታማሚ ቁጥር እያሻቀበ ነው::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012  ብራዚል ኮሮናቫይረስ ከቁጥጥሬ ውጭ አይደለም ብትልም በቀን ውስጥ የሚመዘገበው የሟችና የታማሚ ቁጥር እያሻቀበ ነው::
የፕሬዚዳት ዣየር ቦልሶናሮ የፅህፈት ቤት ሀላፊ ዋልተር ብራጋ ኔቶ በሰጡት መግለጫ በሀገራችን ኮቪድ 19 ቀውስ ፈጥሮብናል ግን ደግሞ ከቁጥጥራችን አልወጣም ማለታቸው ብዙዎቹን አስገርሟል ነው የተባለው፡፡ ምክንያቱም ሀላፊው ይህን አይነት መግለጫ የሰጡት በብራዚል በ24 በሰዓታት ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ ሞትና ከ37 ሺህ በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በተመዘገቡ ማግስት ነው፡፡ የፓን አሜሪካ የጤና ድርጅት ግን ብራዚል ምንም አይነት የመሻሻል ምልክት ያላሳየች ሀገር መሆኗን በመጥቀስ ባለስልጣናቱን አስጠንቅቋል፡፡ የተባበሩት መንግስታ ድርጅት ሪፖርትም የሚያሳየው ብራዚል በቀዳሚነት ሌሎች የላቲን አሜሪካ ሀገራት በተከታይነት ትልቅ ትኩረት የሚሹና ችግሩ የተባባሰባቸው መሆኑን ነው ሲል አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡ ብራዚል በአሁኑ ጊዜ ከአሜሪካ ቀጥላ ብዙ ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ የሞቱባት ሀገር ስትሆን እስካሁን 45 ሺህ 456 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ መሞታቸው ተረጋግጧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *