loading
ብአዴን የድርጅቱን ስም እና አርማ ሊቀይር መሆኑን ገለፀ

አርትስ 03/01/2011
የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት በዛሬው እለት እንዳስታወቀው፥ ብአዴን ትግሉ የደረሰበትን ደረጃ መሰረት በማድረግ የድርጅቱን ስም እና አርማ ሊቀይር ነው።
በዚህም መሰረት ድርጅቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመ የምርጫ ስያሜዎች በአባላት ሙሉ ተሳትፎና ምርጫ በጉባኤ ውሳኔ ለመቀየር በሁሉም የድርጅቱ መዋቅሮች ለውይይት እንዲወርድ ተደርጓል ብሏል።
ለምርጫ የቀረቡት ስሞች ይፋ ሆነዋል፡፡
1. የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አህዴፓ)
2. የአማራ ክልል ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነት ፓርቲ (አህዴአፓ)
3. የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (አህዴድ)
4. የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አህዴን) የሚሉ መሆናቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *