loading
ቦርዱ በሰኔ 14 በተለያዩ ምክንያቶች ድምጽ የማይሰጥባቸውን  አካባቢዎች ይፋ አደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013 ቦርዱ በሰኔ 14 በተለያዩ ምክንያቶች ድምጽ የማይሰጥባቸውን  አካባቢዎች ይፋ አደረገ:: የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በሰኔ 14 በተለያዩ ምክንያቶች የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ የማይከናወንባቸውን  የተወሰኑ አካባቢዎች ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድምጽ መስጫ ቀን
መሆኑን አሳውቆ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል፣ ከዚህም መካከል በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ የድምጽ አሰጣጡ በእለቱ የማይከናወንባቸው ምርጫ ክልሎች መኖራቸውን እና ምክንያታቸውን በግንቦት 14 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ማሳወቁ ይታወሳል ።

ቦርዱ የድምጽ መስጫ ቀን እስኪቃረብም ድረስ እነዚህን ምርጫ ክልሎች ሁኔታ እየገመገመ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን ማቅረብ የሚቀጥል ይሆናል ብሏል።
በዚህም መሰረት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከዚህ በፊት የተጠቀሱት አራቱም (መተከል፣ ሺናሻ ልዩ፣ ካማሽ እና ዳለቲ) የምርጫ ክልሎች ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድምጽ የመስጠት ተግባር አይከናወንባቸውም፣ ቦርዱ ተጨማሪ የአፈጻጸም ሁኔታዎችን ለወደፊት የማሳውቅ ይሆናል ሲል ገልፅዋል።

በሶማሌ ክልል 14 ምርጫ ክልሎች ላይ ሰኔ 14 ቀን 2013 ድምጽ የመስጠት ሂደት ለማካሄድ አስቸጋሪ ይሆናሉ የተባሉ ሲሆን ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ ላይ የታየ መጠነ ሰፊ የአሰራር ችግር አለ በሚል የቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ የአጣሪ ቡድን አሰማርቼ የማጣራት ተግባሬን አጠናቅቂያለሁ ያለ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት የአጣሪ ቡድኑን ግኝት መሰረት አድርጎ ድምጽ መስጠት ሊከናወንባቸው የሚችል ምርጫ ክልሎች ካሉ ለይቶ እንደሚያሳዉቅ ገልፅዋል።
ቦርዱ በኦሮሚያ ክልል ሰባት ምርጫ ክልሎች (ቤጊ፣ ሰኞ ገበያ፣ አያና፣ገሊላ፣አሊቦ፣ጊዳሚ፣ ኮምቦልቻ) ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድምጽ የመስጠት
ተግባር አይከናወንባቸውም ብሏል።

በአማራ ክልል ከዚህ በፊት ከተጠቀሱት ስምንት ምርጫ ክልሎች መካከል ድልይብዛ ምርጫ ክልል ላይ ቦርዱ ሰኔ 14 ቀን 2013 ድምጽ መስጠት ሂደት አንዲከናወን ወስኗል። በሌላ በኩል ግን በአማራ ክልል አንኮበር የምርጫ ክልል ድምጽ መስጠት ሰኔ 14 ቀን እንደማይካሄድም ቦርዱ ወስኗል፣

በደቡብ ክልል ከዚህ በፊት ከተጠቀሱት አራት የምርጫ ክልሎች በተጨማሪ ማጀት መደበኛ የምርጫ ክልል ሰኔ 14 ቀን ድምጽ አይሰጥበትም፤ ይህም የሆነበት ምክንያት በሱርማ፤ በዲዚ፣ በሜኢኔት ልዩ የሚኖሩ ከብሔሩ ውጪ ያሉ ዜጐች ለተወካዮች ም/ቤት በማጀት መደበኛ ላይ ድምፅ ስለሚሰጡ እና የተጠቀሱት ቦታዎች ምዝገባ ስላልተከናወነ ነው ተብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ ጉራፈርዳ ላይ ባለው የጸጥታ ችግር የተነሳ የጸጥታ ችግር ሸኮ ልዩ የምርጫ ክልል እና ቴፒ ምርጫ ክልል  ሰኔ 14 ቀን ድምጽ መስጠት አይከናወንም። በዚህም ምክንያት ደ/ብ/ብ/ህ ክልል ሰባት ምርጫ ክልሎች ላይ በእለቱ ድምጽ አይሰጥም ሲል ቦርዱ በላከልን መግለጫ አስተዉቋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *