loading
ተጠባቂው የቀያዮቹ ትንቅንቅ ጨዋታ ዛሬ ይካሔዳል ።

ተጠባቂው የቀያዮቹ ትንቅንቅ ጨዋታ ዛሬ ይካሔዳል ።

የ27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ከአርብ ጀምሮ እየተካሄዱ ነው፡፡

 

 

ዛሬ የሳምንቱ መርሀግብር ተጠባቂ ግጥሚያ በምንግዜም ተቀናቃኞቹ ማንችስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል መካከል አመሻሽ 11፡05 ላይ ኦልድ ትራፎርድ ላይ ይጫወታሉ፡፡

 

 

ይህ የቀያዮቹ ደርቢ የተቀናቃኞች አሊያም የሰሜን ምዕራብ ደርቢ የሚል ስያሜ የሚሰጠው ሲሆን ዛሬ 202ኛ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ፡፡

 

 

በዚህ ጨዋታ ዩናይትዶች የጄሴ ሊንጋርድ እና አንቶኒ ማርሽያል ከጉዳት አገግሞ መመለስ ይጠብቃሉ፤ ዳቪድ ዴ ሂያ ከኤፍ ኤ ጨዋታ እረፍት በኋላ ይሰለፋል፡፡

 

 

በመርሲ ሳይዱ በኩል ደግሞ በቅጣት ምክንያት የቻምፒዮንስ ሊጉ ጨዋታ በቅጣት ምክንያት ያመለጠው ቨርጂል ቫን ዳይክ ለዛሬው ግጥሚያ ይሰለፋል፡፡

 

 

ተከላካዩ ደያን ሎቭረን በቋንጃ ጉዳት አሁንም ከጨዋታው ውጭ ነው፡፡

 

ማንችስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል ጋር ባደረገው የሜዳው ላይ ዘጠኝ የባለፉት ጨዋታዎች፤ በሰባቱ ድል አድርጓል፡፡

 

 

በተመሳሳይ ሰዓት ሌላኛው የፕሪምየር ሊጉ ግጥሚያ ኤመሬትስ ላይ በአርሰናል እና ሳውዛምፕተን መካከል ይደረጋል፡፡

 

 

ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች በርንሌ ቱርፍ ሞር ላይ ቶተንሃምን 2 ለ 1 ድል አድርጓል፤ ክሪስታል ፓላስ 4 ለ 2 ሌስተር ሲቲ፣ ኒውካስትል 2 ለ 0 ሀደርስፊልድ ሲረቱ፤ በርንማውዝ ከወልቭስ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡

 

ማንችስተር ሲቲ አንድ ጨዋታ ቀደም ብሎ ተጫውቶ ሊጉን በ65 ነጥቦች ይመራል፤ ሊቭፑል በተመሳሳይ ነጥብ በግን ክፍያ አንሶ ይከተላል፡፡ ቶተንሃም በ60 ነጥብ ሶስተኛ፣ ማንችስተር ዩናይትድ በ51 አራተኛ፣ አርሰናል በ50 አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቼልሲ በተመሳሳይ 50 ነጥብ በግብ አንሶ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *