loading
ቱርክ ምዕራባውያን ሀገራትት በዩክሬን ጉዳይ ሽብር የመንዛት ዘመቻቸውን ሊያቆሙ ይገባል ስትል አሳሰበች፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 ቱርክ ምዕራባውያን ሀገራትት በዩክሬን ጉዳይ ሽብር የመንዛት ዘመቻቸውን ሊያቆሙ ይገባል ስትል አሳሰበች፡፡ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ምዕራባውያን ሀገራት በዩክሬን ሁኔታ ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ መግለጫዎችን ከመስጠት መቆጠብ አለባቸው ብለዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስተያየት የተሰማው ሩሲያ በዩክሬን ላይ በማንኛውም ጊዜ ጥቃት ልትፈፅም ትችላለች በማለት አሜሪካ ካስጠነቀቀች በኋላ ነው።


እንዲህ ዓይነቱ ወረራ ትክክል አይደለም ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የምዕራባውያን ሀገራት ሽብር የሚፈጥሩ መግለጫዎችን ከማውጣት መቆጠብ አለባቸው ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ካቩሶግሉ በሩሲያና በዩክሬን መካከል ለሚፈጠረው ቀውስ ዝግጁ መሆን እንደሚያስፈልግ የጠቀሱ ቢሆንም ቱርክ ፍርሀት ውስጥ እንደማትገኝ ገልፀዋል ሲል ሚድል ኢስት ሞኒተር አስነብቧል። ሩሲያ በቅርቡ በዩክሬን አቅራቢያ ከ100 ሺህ በላይ ወታደሮችን ማከማቸቷን ተከትሎ በጎረቤቷ ላይ
ወታደራዊ ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች የሚል ስጋት ተፈጥሯል፡፡


ሞስኮ ለወረራ እየተዘጋጀች ነው የሚለውን የምዕራባውያን ሀገራት ክስ ውድቅ ያደረገች ሲሆን የኔቶ ወደ ድንበሯ መስፋፋት ለደህንነቷ እያሰጋት እንደሆነ ተናግራለች።
ሩሲያ ለምዕራቡ ዓለም የጸጥታ ጥያቄዎችን ዝርዝር ያቀረበች ሲሆን ወደ አንዳንድ የቀድሞ የሶቪየት መንግስታት የተላኩ ወታደሮች ወደ ኋላ እንዲመለሱና ዩክሬን እና ጆርጂያ ኔቶን እንደማይቀላቀሉ ዋስትና እንዲሰጣት የሚሉት ይገኙበታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *