loading
ታላቁን ቤተ መንግሥት ወደ ሙዚየምነት ለመቀየር የፈረንሣይ መንግሥት ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባ

ታላቁን ቤተ መንግሥት ወደ ሙዚየምነት ለመቀየር የፈረንሣይ መንግሥት ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባ

አርትስ 19/02/2011

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤትና መኖሪያ የሚገኝበትን የአፄ ምኒልክ ቤተ መንግሥት በዘመናዊ መንገድ በማደስና በማልማት ወደ ሙዚየምነት ለመቀየር፣ የፈረንሣይመንግሥት ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱ ታውቋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶር) ሐሳብ አመንጪነት ታላቁን የምኒልክ ቤተ መንግሥት በማደስና ተጨማሪ ልማቶችን በማከናወን፣ ለሕዝብና ለጎብኝዎች ክፍትየሚሆን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ዕቅድ ተይዟል፡፡

ይህንንም በፍጥነት በተግባር ለመቀየር የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ሚኒስቴር ኃላፊነት ተሰጥቶታል።

ፕሮጀክቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸው በበላይነት እየተከታተሉት እንደሚገኙም ታውቋል። በዚህም መሠረት የተለያዩ አገሮች ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኝነታቸውን እንዳሳዩ፣በዋናነት ግን የፈረንሣይ መንግሥት አስፈላጊውን የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱን ሪፖርተር ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግንቦት ወር 2010 ዓ.ም. በውጤታማ ሥራ አፈጻጸም ላይ በወቅቱ ለነበሩ የካቢኔ ሚኒስትሮች ባደረጉት ገለጻ፣ የአፄ ምኒልክ ቤተ መንግሥትን የቱሪዝምመዳረሻ ማድረግ እንደሚገባ መግለጻቸው ይታወሳል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *