loading
ቴህራን እንኳንስ ለራሴ ለሰውም እተርፋለሁ እያለች ነው

ቴህራን እንኳንስ ለራሴ ለሰውም እተርፋለሁ እያለች ነው

አርትስ 18/03/2011

ኢራን በሀገሯ ልጆች በተሰሩ የጦር መሳሪያዎች ከጠላቶቿ ራሷን ለመከላከል ተዘጋጅታለች፡፡

የኢራን ሳይንቲስቶች ድካማቸው ፍሬ አፍርቶ በአየርም በባህርም ለሀገራቸው ዘብ የሚቆሙ ተዋጊ ጀቶችና ባህር ሰርጓጅ የጦር መርከቦችን ሰርተው ዝግጁ አድርገዋል፡፡

ጠኢራን የአቬስን ኢንደስትሪ ሀላፊ ብርጋዴር ጄኔራል አብዱከሪም ባኒታራፊ እንደሚሉት ኢራን ከራሷ አልፋ የሀገር ልጆች እጅ ጥበብ ውጤቶች የሆኑትን ጀቶች ኤክስፖር ለማድረግ ተዘጋጅታለች፡፡

ፕሬስ ቴሌቭዥን እንደዘገበው ኢራን በአሁኑ ወቅት ከቻይና፣ ከሩሲያና ከኢንዶኔዥያ ጋር የገበያ ስምምነት ላይ ደርሳለች፡፡

አሁን ላይ እነዚህን ምርቶች ለሚፈልጉ ሀገራ ለመሸጥ ፈቃድ ስለተሰጠን  ከጥቂት ጊዜ በኋላ ለገበያ ለማቅረብ ዝግጅታችንን አጠናቀናል ብለዋል ጄኔራሉ፡፡

የኢራን የመከላከያ ሚኒስትር ብርጋዴር ጄኔራል አሚር ሀታሚ ኢኮኖሚያዊ ማእቀብ ቢጣልብንም እጅ ሳንሰጥ በሁሉም መስኮች በስኬት እየተጓዝን ነው ብለዋል፡፡

ኢራን  በሀገር ውስጥ ተሰርተው ለውጊያ ዝግጁ የሆኑ የባህር ሰርጓጅ ጦር መርከቦችን በፈረንጆቹ 2019 ይፋ ለማድረግ መዘጋጀቷንም አስታውቃለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *