loading
ትሪፖሊ ለጄኔራል ሀፍታር የእንወያይ ግብዣ አቀረበች፡፡

ትሪፖሊ ለጄኔራል ሀፍታር የእንወያይ ግብዣ አቀረበች፡፡

የምስራቁን የሀገሪቱን ክፍል የተቆጣጠረው የጄኔራል ሀፍታር ጦር ትሪፖሊን ለመያዝ የሚያደርገውን ግስጋሴ አጠንክሮ በቀጠለበት ወቅት ዓለም አቀፍ እውቅና ከተሰጠው ከትሪፖሊ መንግስት ችግሩን በሰላም እንፍታው የሚል ጥሪ ቀርቦለታል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው የሊቢያ የውጭ ጉዳይ ሚነስትር ሞሀመድ ሳላህ በሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች መካከል የተጀመረው ውጊያ ማብቃት አለበት ነው ያሉት፡፡

ሳላህ አክለውም ጦርነቱ እንዲቆም እና ሰላም እንዲፈጠር ከሁሉም አጋሮቻችን ጋር እየመከርንበት ነው ብለዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ የሰላም ጥረቱ ከአንድ በኩል ብቻ እንዳይሆን የጄኔራል ሀፍታር ሰዎችም እንዲያስቡበት እና ለሰላም ጥሪው መልከም ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *