loading
ትራምፕ እንዲከሰሱ ድምፅ የሰጡት ተወካይ በምርጫ መሸነፍ…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2014 በካፒቶል ህንፃ በተነሳው ግርግር ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዲከሰሱ ድምፅ የሰጡት የሪፓበሊካን ተወካይ በዳግም ምርጫ ተሸነፉ፡፡ በኖርዝ ካሮላይና ለአምስት ዓመታት በህግ አውጭ ምክር ቤት ተወካይነት ያገለገሉት ቶም ራይስ የተሸነፉት በቀድሞው ፕሬዚዳንት በሚደገፉት ሩሴል ፍራይ በተባሉ እጩ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡


ፍራይ ማሸነፋቸውን ካወቁ በኋላ ባደረጉት ንግግር መራጩ ህዝብ በግልፅ ቋንቋ በካርዱ ተናግሯል፤ ራይስ ሆይ ወደቤትዎ ይመለሱ መልካም መንገድ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ በቀጣዩ አጠቃላይ ምርጫ የማሸነፍ ግምት የተሰጣቸው ፍራይ በደጋፊዎቻቸው ፊት ዛሬ ዶናልድ ትራምፕ አሸንፈዋል ማለታቸውንም ዘገባው አክሎ ገልጿል፡፡


ይህም በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ተሸንፈው በውዝግብ ነጩን ቤት ለለቀቁት ዶናልድ ትራምፕ የበቀል እርምጃ መልካም ጅምር ተደርጎ ተወስዷል ነው የተባለው፡፡ትራምፕ ከአሁን ቀደም ተሸናፊውን ቶም ራይስን ጨምሮ ይከሰሱ ብለው ድምፅ በሰጡ 10 የሪፓብሊካን ፓርቲ ተወካዮች ለበቀል መግዛታቸው ይታወሳል፡፡
ቶም ራይስ በትራምፕ ላይ የይከሰሱ ድምፅ ከሰጡት የሪፓብሊካን ፓርቲ ተወካዮች መካከል የመጀመሪያው ተሸናፊ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ላለመወዳደር መወሰናቸው ተሰምቷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *