ትራምፕ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉትን ስብሰባ ሊሰርዙት እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጡ
አርትስ 19/03/2011
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን በቡድን 20 ሀገራት ጉባኤ የጎንዮሽ ስብሰባ ለማድረግ ቀጠሮ ተይዞላቸው ነበር፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ግን ሩሲያ በዩክሬን መርከቦች ላይ የፈጸመቸው የትንኮሳ ተግባር ስላናደደኝ ከፑቲን ጋር የነበረኝን ቀጠሮ ልሰርዘው እችላለሁ ብለዋል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው አሜሪካ የአወሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ዩክሬንን ለመደገፍ ብዙ መስራት ይጠበቅባቸዋል የሚል አቋም አላት፡፡
ዋሽንግተን በሩሲያ ላይ ጠበቅ ያለ ማእቀብ ተግባራዊ እንዲሆን ትፈልጋለች ያሉት ደግሞ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሄዘር ናወርት ናቸው፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፒዮ በበኩላቸው የሩሲያ ድርጊት ዓለም አቀፍ ህግን የሚጥስና የአንዲትን ሀገር ሉዓላዊነት የሚጋፋ ነው ብለዋል፡፡
ፕዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደግሞ ለተፈጠረው ነገር ሁሉ ተጠያቂዋ ዩክሬን ናት እኛም ሁኔታው በቀላሉ አንመለከተውም ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡፡