loading
ትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ ከመደበችው በጀት 40 በመቶውን ለክትባት ታውላለች አሉ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2012 ኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ ከመደበችው በጀት 40 በመቶውን ለክትባት ታውላለች አሉ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፡፡
ፕሬዝደንቷ ይህን ያሉት የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በጠሩት ዓለም አቀፍ የክትባት ጉባኤ ላይ ላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ ከመደበችው በጀት መካከል በዚህ መጠን ለማዋል መነሳቷ መንግስት ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት መስጠቱን እንደሚያሳይ ተናግረዋል፡፡ የበርካታ ሀገራትና መንግሥታት መሪዎች በተሳተፉበት እና በቪድዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው ጉባኤ ላይፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ሲናገሩ ኮቪድ-19 ን ለመቆጣጠር ለሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት
የጉባኤው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ብለዋል።ከ20 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ከ30 በመቶ በታች የነበረው የክትባት ሽፋን መንግሥት በሰጠው ትኩረትና በአጋሮች ድጋፍ 72 በመቶ መድረሱንና ለክትባት የሚመደበው ከጤናው ዘርፍ በጀት 40 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል። በሀገሪቱ አነስተኛ ሽፋን የሚታባይባቸውን አካባቢዎች በመለየትም የክትባት ሽፋኑን የሚፈለግበት ደረጃ ለማድረስ መንግስት የያዘውን ከፍተኛ ቁርጠኝነት አብራርተዋል። ዓለም በኮቪድ-19 የተነሳ ለገጠማት ችግር መፍትሔ ፍለጋችን ከውድድር ይልቅ ትብብርን ማስቀደም  እንደሚገባና የክትባቱ ሥርጭት ደሃና ሃብታም አገሮችን መለየት እንደሌለበት ማሳሰባቸውን
የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት አስታውቋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *