loading
ቶጎ በምዕራብ አፍሪካ ግዙፍ የተባለውን የፀሃይ ሃይል ማመንጫ ይፋ አደረገች::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22፣ 2013 ከዋና ከተማዋ ቶጎ በደቡባዊ አቅጣጫ 250 ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኝው ይህን ፕሮጀክት የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡ ፕሮጀክቱ 158 ሺህ የሚሆኑ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን በቀጣይ ለማዳረስ ዕቅድ ተይዞለታል ነው የተባለው፡፡

በአቡዳቢው ልኡል ሼክ ሙሃመድ ቢን ዛይድ የተሰየመው ይህ ፕሮጀከት 64 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር በሆነ የብድር ገንዘብ መሰራቱም ተነግሯል፡፡ ብድሩ ከምዕራብ አፍሪካ የልማት ባንክና ከአቡዳቢ የልማት ፈንድ ማገኘቱ አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አስነብቧል፡፡ የዱባዩ የልማት ድርጅት ሊቀመንበር ሃሰን ጃስም አልናዋሲ ቶጎ ከፍተኛ የተፈጥሮ ሃብትና የፀሃይ ሃይል ያላት ሀገር በመሆኗ ይህ አጋጣሚ ለታዳሽ ሃይል ልማት መልካም ዕድል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ቶጎ 8 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎቿ ከዚህ ቀደም ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የኤሌክትሪክ ፍጆታ ከናይጄርያና ከጋና ታገኝ እንደነበረ ይታወቃል፡፡

አዲሱ ፕሮጀክት በ18 ወራት ወስጥ የተጠናቀቀ ሲሆን ለምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ መነቃቃትን እንደሚፈጥር ታምኖበታል ፡፡ቶጎ በአመቱ ማጠቃለያ 127 ሺ 344 የፀሃይ ሃይል ማመንጫ ፓናሎችን በማምረት 90 ነጥብ 255 ሜጋዋት በሰዓት ለማምረት ዕቀድ ማስቀመጧን ገልፃለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *